የአካይ ልዩ ምንጣፍ
Ursula Nafula
Catherine Groenewald

አካይ ትንሽ ልጅ እያለች እናቷ በሚያምር ምንጣፍ ላይ ታስተኛት ነበር። ይህን ልዩ ምንጣፍ ከዘንባባ ቅጠሎች የሰራችው የአካይ አክስት ነች።

1

ምንጣፉ ደማቅ ሮዝ፣ ሰማያዊ እና አረንጓዴ ቀለሞች ነበሩት፡፡ የአካይ እናት ጎጆዋ ውስጥ ከነበሯት ሌሎች ምንጣፎች የተለየ ነበር።

2

በአካይ ቤት ዙሪያ ያለው መሬት በጣም ደረቅ፣ ሞቃትና እና በድንጋይ የተሞላ ነበር። ብዙ ጊንጦች፣ ሸረሪቶች እና እባቦችም ነበሩ። ነገር ግን አካይ በእነዚህ አደገኛ ፍጥረቶች የመነከስ አደጋ ፈጽሞ አልነበረባትም።

3

እናቷ ‹‹አካይ፣ ይህ ልዩ ምንጣፍሽ ከማንኛውም ጉዳት ይጠብቅሻል›› አለቻት፡፡

4

አካይ ጎበዝ ልጅ ነበረች። ጥልቀት የሌለው ጉድጓድ በቅርቡ የት እንዳለ ለማወቅ ቻለች።

5

አካይ የአያትዋ ማኒያታ የት እንዳለ ታውቃለች። ብዙ ጊዜ የግመል ወተት ልትጠጣ ወደ ሴት አያቷ ቤት ትሄድ ነበር።

6

አካይ አንድ ቀን በጣም እድሏ ሳይቃና ቀረ። ወደ አያቷ ማኒያታ አመራች፤ ይሁን እንጂ በመንገድ ላይ ሳለች በኮረብታው ላይ ጠፋች። አካይ ፈራች።

7

ከኤዶም ዛፍ ስር ተቀምጣ የሚረዳትን ለማግኘት ትጠባበቅ ነበር፡፡ ብዙም ሳይቆይ እንቅልፍ ያዛትና ህልም አየች።

8

አካይ ያለመችው እንዲህ ነው። በልዩ ምንጣፏ ላይ ተኝታ ሳለች ሴት አያቷን የምትመስል ሴት ትጠብቃታለች። አሮጊቷ ሴትዮ ፈገግ ብላ አንድ ሳህን የግመል ወተት ሰጠቻት። አካይ ወተቱን ለመውሰድ እጇን እንደዘረጋች ነቃች።

9

አካይ አይኖቿን በቀስታ ገለጠች። ቀና ብላ ስትመለከት ከእሷ በላይ ባለው ቅርንጫፍ ላይ ትንሽ ሰማያዊ ወፍ አየች።

10

አካይ ስትነሳ ትንሿ ሰማያዊ ወፍ ክንፎቿን ዘርግታ አካይን መንገድ ትመራት ጀመር። ልጅቱም ወፏን ተከተለቻት።

11

አካይ መንገዱ ወደ ሁለት የተለያዩ አቅጣጫዎች ከሚከፈሉበት ቦታ ደረሰች። ሰማያዊዋ ወፍ የአካይን ምንጣፍ የመሰለ ነገር ጣለች።

12

ምንጣፉን እያነሳች ሳለች፣ አካይ የእናቷ መሆናቸውን ያመነችባቸውን አሻራዎች አየች። ወዲያውኑም ውሃ የሚቀዱበትንና ጥልቀት የሌለውን ጉድጓድ አየች።

13

የአካይ ቤተሰብ ልጃቸው ወደ ቤታቸው ስትመጣላቸው ለመቀበል ይዘፍኑና ይጨፍሩ ጀመር። ፍየል አርደውና ስጋውን ጠብሰው የልጃቸውን በሰላም መመለስ አከበሩ።

14

አካይም በልዩ ምንጣፏ ላይ ተቀምጣ ትልቅ የተጠበሰ ሥጋ በመብላት ትደሰት ጀመር።

15
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የአካይ ልዩ ምንጣፍ
Author - Ursula Nafula
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Catherine Groenewald
Language - Amharic
Level - First paragraphs