ኤሊዎች ለምን ፀጉር እንደሌላቸው
Maxwell Abwamba
Maxwell Abwamba

በአንድ ወቅት ሊኩቱ የተባለ ኤሊ ይኖር ነበር፡፡ ሊኩቱ ከአንድ ገበያ አጠገብ ነበር የሚኖረው፡፡

በዚህ የገበያ ስፍራም አንዲት ማንዳዚ እየጠበሰች የምትሸጥ ሴት ነበረች፡፡ ብዙ ሰዎች ከእርሷ ለመግዛት ይሰለፋሉ፡፡

የማንዳዚው መዓዛ ሊኩቱን አማለለው፡፡ ጥቂት ለመግዛትም ተመኘ፡፡

1

2

አንድ ቀን ሊኩቱ ማንዳዚ ወደምትሸጠው ሴት ሄደ፡፡ ‹‹ጥቂት ማንዳዚ ለማግኘት ለእርስዎ አንድ ነገር የማደርግልዎት ነገር አለ?›› በማለት ጠየቃት፡፡

‹‹አዎ፣ ወደ ቻማ የሴቶች ቡድን ስሄድ፣ ሱቄን እንድታይልኝ›› ስትል ሴትየዋ መለሰችለት፡፡

3

4

ሴትዮዋ በሌለችበት ጊዜ ሊኩቱን አንድ የሚያብረቀርቅ ማንዳዚ ማረከው፡፡

በደስታም ለራሱ ‹‹የምችለውን ያህል እበላና የተወሰኑትን በባርኔጣዬ ውስጥ እደርጋለሁ›› አለ፡፡

5

6

ሊኩቱ ከራሱ ጋር ማውራቱን ገና ሳይጨርስ ባለማንዳዚዋ ሴትዮ ከሩቅ ብቅ ስትል አያት፡፡

እየፈላ ከነበረው ዘይት ውስጥ ያወጣውን ማንዳዚ በባርኔጣው ጠቀጠቀ፡፡

ከዚያም ባርኔጣውን ጭንቅላቱ ላይ አደረገ፡፡ ወዲያውኑ ሊኩቱ በሚያቃጥለው ማንዳዚ ምክንያት አንገቱን ማዟዟር ጀመረ፡፡

7

8

ሴትዮዋ እንደደረሰች ልጁ በህመም በጣም ሲንጠራራ ስትመለከተው ተገረመች፡፡

እሷም ‹‹ምነው የሆነ ችግር አለ?›› በማለት ጠየቀችው፡፡

‹‹አይ ምንም ችግር የለም!›› ሲል ሊኩቱ መለሰላት፡፡

በፍጥነት ወደ አጎቱ ልጅ ቤት ሄደ፡፡

የአጎቱን ልጅ ከእንግዶች ጋር ስላገኘው ዉጪ ቁጭ ብሎ ጠበቀው፡፡

9

10

ሊኩቱ እየጠበቀ ሳለ አንገቱን መወዝወዙን ቀጠለ፡፡

የሊኩቱ የአጎት ልጅ አንገቱን ሲወዘውዝ ሲያየው ግራ ተጋባ፡፡

ብቅ ብሎም የሊኩቱን ባርኔጣ አነሳው፡፡ ማንዳዚው መሬት ላይ ተዝረከረከ!

11

ሁሉም የሊኩቱ ፀጉር ተቃጥሏል፡፡ ልጁ መላጣ ሆኗል፡፡

‹‹እንዴ፣ ምን ሆንክ?›› የአጎቱ ልጅ ጠየቀ፡፡ ሊኩቱ ግን ለመናገር በጣም አፍሮ ዝም አለ፡፡

የሊኩቱ ፀጉር ዳግመኛ አላደገም፡፡

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ኤሊዎች መላጣ ሆነው ቀሩ።

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ኤሊዎች ለምን ፀጉር እንደሌላቸው
Author - Maxwell Abwamba
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Maxwell Abwamba
Language - Amharic
Level - Longer paragraphs