ሁሉንም ቀለማት ብሉ!
Mimi Werna
Pixabay Website

ፍራፍሬዎችን ስትበሉ ቀለሞችን እየበላችሁ እንደሆነ ታውቃላችሁ?

1

ፖም ምን ዓይነት ቀለም አለው?

ሁሉንም ዓይነት ፖም ብሉ፡፡

አረንጓዴ፣ ቀይ፣ ቢጫ እና ሮዝ ፖም ብሉ!

2

ኮኮናት ምን ዓይነት ቀለም አለው?

እያንዳንዱን ዓይነት ኮኮናት ብሉ ፡፡

ትኩስ የኮኮናት እና የደረቀ ኮኮናት ተመገቡ፡፡

3

ብርቱካናማ ቀለም ያለው የትኛው ፍራፍሬ ነው?

ብርቱካን አረንጓዴው ቀለም የሚኖረው መቼ ነው?

4

ሐብሐብ ሮዝ ቀለም አለው፡፡

ሮዝ የእኔ ተወዳጅ ፍሬ ነው!

ፍራፍሬዎችን ስትመገቡ ቀለሞችን ትበላላችሁ፡፡

5

አቮካዶ አንድ ትልቅ ፍሬ ብቻ አለው፡፡

አቮካዶ ስትመገቡ ምን ዓይነት ቀለም እየበላችሁ ነው?

6

እነዚህ ቃሪያዎች ምን ዓይነት ቀለም አላቸው?

እያንዳንዱ ዓይነት ቃሪያ ፍሬ ነው፡፡

ፍራፍሬዎች ከአትክልቶች የተለዩ ናቸው፡፡

7

ፍራፍሬዎች በአንድ ተክል ላይ ከአበቦች ቀጥለው ያድጋሉ፡፡

ፍራፍሬዎች ዘሮች አሏቸው፡፡

የትኞቹን ፍራፍሬዎች መመገብ ትፈልጋላችሁ?

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሁሉንም ቀለማት ብሉ!
Author - Mimi Werna
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Pixabay Website
Language - Amharic
Level - First sentences