

ከእለታት አንድ ቀን ከአንዲት ትንሽ መንደር አቅራቢያ ባለ አነስተኛ የእርሻ ቦታ ላይ፡፡
ዴይዚ የተባለች ትንሽ ዶሮ ትኖር ነበር።
ዴይዚ "ሳድግ እየበረርኩ ወደ ሰማይ መውጣት እፈልጋለሁ" አለች፡፡
ነገር ግን ሌሎች ዶሮች በሙሉ ሳቁባት፡፡
ከዛም ዶሮዎቹ እኛ ከአንቺ ጋር አንጫወትም ፡፡ አንቺ አብደሻል አሏት።
" ዴይዚ, ሁላችንም ያሉንን ክንፎች ማራገብ እንችላለን ነገር ግን መብረር ለዶሮዎች በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡"ብለዉ እናቷ ነገራት.
ዳይዚ ተስፋ አልቆረጠችም። በየዕለቱ ክንፎቿን በማራገብ እራሷን ታለማመድ ነበር፡፡ ክንፎቿን አርገበገበች አርገበገበች አርገበገበች ቢሆንም ግን ከምድር ላይ ማንሳት አልቻለችም።
እየተለማመደች በነበረችበት ጊዜ እራሷን ወደ ላይ ወደ ሰማይ እንደሚበር እና ከታች ያሉትን ዶሮዎችን እየተመለከተች መሰላት፡፡ ድንቢጦችን እና ዋጦችን አልፋ እየበረረች እንደሆነ አስባለች። "ዋዉ! የሚበር ዶሮ!" እያሉ መሰላት።
ዴይዚ ክንፎቿን በየቀኑ ማርገብገቧን በርትታ ቀጠለች፡፡
ከመሬቱ ላይ ትነሳና እንደገና ትወድቃለች።
"በፍፁም ልበር አልችልም!" ብላ ዴይዚ እናቷ ጋር ሄዳ አለቀሰች። "ሌሎች ትክክል ናቸው ዶሮ መብረር አይችልም።" አለች።
"ዴይዚ አንቺ ከሌሎቹ ዶሮዎች የተለየሽ ነሽ። እነሱ መብረር አይፈልጉም አንቺ ግን ማድረግ ትችያለሽ" አለቻት እናቷ።
በማግስቱ ዴይዚ ወደ ዶሮ ማቆያው አናት ላይ ወጣች እና ክንፎቿን እንደተለመደው ማርገብገብ ጀመረች። ወደ አየር በረረች እና ክንፎቿን እጥፍ ዘርጋ እጥፍ ዘርጋ ለማድረግ ብትሞክርም።
ዘጭ! ብላ ወደቀች።
ሌሎቹ ዶሮዎች ጮክ ብለው እየሳቁ። "ሃሃሃ! ነግረንሽ ነበር ዶሮ አይበርም!" እያሉ ተሳለቁባት።
ነገር ግን በማግስቱ ዴይዚ እስከ ጎጆው ጫፍ ድረስ ከፍ ብላ ወጥታ። ክንፎቿን እንደገና ማርገብገብ ጀመረች።
ወደ አየር በረረች እና ክንፎቿን በደንብ ማርገብገቧን ቀጠለች።
መብረሯን ቀጠለች! ከክንፎችዋ በታች ያለው ንፋስ እየበረታ ሄደ እና ከፍ ከፍ ብላ ትበር ጀመረ! ድንቢጦቹ እና ዋሾቹ ሲያዩዋት በመገረም "አስደናቂ ነው! የሚበር ዶሮ!" ተባባሉ።
በስተ መጨረሳም ሌሎቹም ዶሮዎች እንደ እሷ መሆን ፈለጉ፡፡
እነሱም ኦህ ዴይዚ! አንቺ አስገራሚ ነሽ! አሏዋት፡፡
ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ!


