ብልህዋ ሴትዮ
ሰሚራ መሓመድብርሃን
Adonay Gebru

በደሮው ጊዜ፣ ሁለት ጓደኛሞች ነበሩ፡፡ አንዱ ጉበዝ ሲሆን ሌላኛው ሞኝ ነበር፡፡

የሞኙ ሰውዬ ሚስት ብልህ ነበረች፡፡ የጎበዙ ሰውዬ ሚስት ደግሞ ቂል ነበረች፡፡

1

ባሎቹ በሚያወጉበት ጊዜ፣ ጎበዙ ሰውዬ "ያንተ ሚስት ብልህ ናት፡፡ ነገር ግን አንተ ሞኝ ነህ፡፡ የእኔም ሚስት ቂል ናት፡፡ ስለዚህ የእኔ ሚስት ምናልባትም ይበልጥ ለአንተ የምትመጥን ናት" አለው፡፡

2

ሞኙ ሰውዬ "ከእኔ እና ካንተ ማነው በጣም ሞኙ?" ሲል ጠየቀው፡፡ ከዚያም "እኔ እኮ ከአንተ እኩል ጎበዝ ነኝ" አለ፡፡

"እንደዚያ ከሆነ ወደ ዳኛ እንሂድ እና ጥያቄ ልጠይቅህ" ሲል ጎበዙ መለሰ፡፡ ወደ ዳኛ ለመሄድም ተስማሙ፡፡

3

በዳኛ ፊት ሲቀርቡ፣ ጎበዙ ሰውዬ "በሰማዩ ላይ ምን ያህል ኮከቦች አሉ? የዓለም መሃሉስ የት ላይ ነው? ሁለቱን ጥያቄዎች መልስ፣ አለበለዚያ ሚስቶቻችንን እንቀያየር" አለው፡፡

ዳኛውም ለሞኙ ሰውዬ መልሱን አዘጋጅቶ እንዲመጣ ጊዜ ሰጡት፡፡

4

አንድ ቀን ምሽት ላይ ሞኙ ሰውዬ በቤቱ ጣራ ላይ ተቀምጦ ኮከቦቹን እየቆጠረ ነበር፡፡
ሚስቱ "ምን እየሠራህ ነው?" ስትል ጠየቀችው፡፡

5

እሱም "ጓደኛዬ በሰማዩ ላይ ስንት ኮከቦች እንዳሉ እና የዓለም ማህሉ የት ላይ እንደሆነ ጠይቆኛል፡፡ አሁን ኮከቦቹን እየቆጠርኩ ነው" ሲል መለሰላት፡፡

6

ሚስቱ "እትጨነቅ፣ እኔ መልሱን አንግርሃለሁ" አለችው፡፡ ለባልዋ አንድ ስልቻ ጤፍ ሰጠችው፡፡ "በሰማዩ ላይ ስንት ኮከቦች እንዳሉ ከጠየቁህ፣ በስልቻው ውስጥ ካለው ጤፍ ጋር እኩል እንደሆኑ ነገራቸው" አለችው፡፡

7

ከዚያም አንድ ጦር ሰጠችው እና እንዲህ አለችው " የዓለም መሃሉ የት ላይ እንደሆነ ከጠየቁህ፣ ጦሩን በመሬቱ ላይ ሰክተህ፣ የዓለም መሃሉ ይህ ነው በላቸው፡፡ ካልተስማሙ፣ ለክተው እንዲደርሱበት ንገራቸው፡፡"

8

ሞኙ ሰውዬ የሚስቱን ምክር ይዞ በቀጠሮው ቦታ ደረሰ፡፡

መጀመሪያ "የከዋክብቱ ቁጠር በዚህ ስልቻ ውስጥ ካለው የጤፍ ቁጥር ጋር እኩል ነው" ብሎ መለሰ፡፡
ከዚያም ጦሩን በመሬት ላይ ሰካ እና "የዓለም መሃል ይህ ነው" አለ፡፡

9

ዳኛው ተገረመው ነበር እና "ይህን የነገረህ ማን ነው?" አሉት፡፡ ሞኙ ሰውዬም "ሚስቴ" ሲል መለሰላቸው፡፡

ዳኛው ቀጥለው "ሚስተህ በጣም ብልህ ናት፡፡ ስለዚህ ከጉበዝ ጋር መጋባት አለባት፡፡ ሚስትህን ቀይር" አሉት፡፡ ከዚያም ዳኛው ሚስቶቻቸውን ሊያቀያይሯቸው ቀጠሮ ሰጡ፡፡

10

ሞኙ ሰውዬ "ክርክሩን እረትቻለሁ፡፡ ነገር ግን ዳኘው አንችን ብልህ ናት ብለዋል እና የእኔ ሚስት መሆን አይገባሽም" አላት፡፡

ሚስቲቱም "አታስብ፣ ለዚህም ቢሆን ጥሩ መፍትሔ አለኝ" አለችው፡፡

11

ዳኛው ሚስቶቹን የሚያቀያይሩበት ጊዜ ደረሰ፡፡ ብልህዋ ሚስት በጎድጓዳ ሞሰብ ለዳኛው ምግብ በስጦታ አቀረበች፡፡ ዳኛው ሞሰቡን ሲከፍቱት ከእነ ላባዋ የተቀቀለች ዶሮ አገኙ፡፡ ደነገጡ፣ ድምጻቸውን ከፍ አድርገውም "ኦ! ታዘብኳት፣ ይቺ ሴት እዛው ከሞኙ ባልዋ ጋር ትሁን!" ብለው በየኑ፡፡

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ብልህዋ ሴትዮ
Author - ሰሚራ መሓመድብርሃን, ኣብርሃ ተኣምራት
Translation - Kebede Yimer
Illustration - Adonay Gebru
Language - Amharic
Level - Longer paragraphs