

በአንድ ወቅት፣ በጆበርግ ኦሬንጅ ግሩቭ ውስጥ፣ አንዲት ሕፃን ወደዚህ ዓለም መጣች፡፡ ስሟም ፊሊስ ተባለ፡፡ ፍቅረኛሞቹ ወላጆቿም ተወዳጅ ሕፃን ልጃቸውን አቀፏት፡፡ ከዚያ በኋላ እንዴት ዳንሰኛ እንዳደረጓት ማንም ሰው አያውቅም፡፡
የመደነስ ጥበብን በአራት ዓመቷ፣ በፍጥነት ተማረችው፡፡ በእግሮቿ ጣቶች እንደ ዳክየ ስትፈናጠር አስተማሪዋን ሳይቀር ታስደንቀው ነበር፡፡ ትምህርት ቤት ከመሄዷ በፊት እና ስትመለስ አዘውትራ ትደንሳለች፡፡ ከባሌት ዳንስ የበለጠ የሚያስደስታት ነገርም አልነበረም፡፡
ፊሊስ በአስራ አምስት ዓመቷ፣ ህልሟን ለማሳካት በለንደን ከተማ ለመኖር ተዘጋጀች፡፡ ለሁሉም ጓደኛቿ "ደህና ሁኑ" ስትል የስንብት ሰላምታ አቀረበች፡፡ በአዲስ መልክ ለመጀመርም ዝግጁ ነበረች፡፡ ፊሊስ ሮያል የባሌት ዳንስ ትምህርት ቤትን ጎበኘች፡፡ በዚህም ተደነቀች፡፡
ፊሊስ የ"ሳዋን ሌክን" ስትደንስ፣ ሥራዋ ለንግስቲቱ ቀርቦ ለመታየት መጣኝ ይሆንላታል! ለዓመታት ከሠለጠነች በኋላም ለሌሎች ተመልካቾች ለማሳየት ተዘጋጀች፡፡ ስታቀርብም ተሽከረከረች፤ እንደእንዝርት ሾረች፡፡ እነሆ! ሁሉም ሰው በፈገግታ ደመቀ! ከልባቸው ጮሁላት፤ አጨበጨቡላት!
ፊሊስ የዳንስ ትርኢቷን ለማሳየት፣ በስፋት ከሜክሲኮ እስከ ከናዳ፣ ከአሜሪካ እስከ ፈረንሳይ ርቃ ተጓዘች፡፡ በዚህም ዓለም ዳንሷን ለማየት ቻለ፡፡ ለባሌት ዳንስ ያላትን ፍቅር ከሮያል የባሌት ዳንስ ድርጅት እና ከባሌት ጓደኞቿ ጋር በመሆን ለባሌት አፍቃሪያን አዳረሰች፡፡ የባሌት ዳንስ ፈጽሞ እንዲቋረጥባትም አትሻም፡፡
ፊሊስ የባሌት አጨፋፈር ጥበብ በልቧ ውስጥ እንዳለ ታውቃለች፡፡ ቢሆንም እንደገና እንዳዲስ ለማጥናት ወደ ቤቷ ለመመለስ ወሰነች፡፡ ስለሆነም ወደ ውቢቷ ሀገሯ ጊዜ ሳታባክን ተመለሰች፡፡ የባሌት ዳንስ ችሎታዋንም እንደገና አደሰችው፡፡ ፊሊስ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜም ደቡብ አፍሪካዊት ሆና ቀረች፡፡
ፊሊስ፣ ዳንስ እንዲሁ ለመዝናኛ ብቻ እንዳልሆነ ታውቃለች፡፡ የመደነስ ጥበብን ቀንም ሆነ ሌሊት ትለማመዳለች፡፡ ጠንክራ በመስራቷም መሻሻል ችላለች፡፡ ሁኔታው መጥፎም ይሁን መልካም ሁሌም ፈገግታ አይለያትም፡፡ ሁሌም ለመሞከር አትሰንፍም፡፡ የተሻለ ለመሥራት የማታደርገው ጥረት የለም ፡፡ ያም ሆኖ አይበቃትም፡፡
ሮሚዮ እና ጁሌት ፣ ስዋን ሌክ እና ጌሊስ የተባሉትን ዘፈኖች፣ ፊሊስ ሳትደክም፣ አሳምራ እና አስውባ ለተመልካቾች ደነሰች፡፡ ከአጋሮቿ ከእነ ጋሪ በርኔ እና ኤድዋርድ ግሬሊንግ ጋር ታዳሚዎችን አነቃቃቻቸው። ለእሷም አበባ በተኑላት፡፡
ራስህን ለፈተና ስታዘጋጅ፣ ሽልማት በቀላሉ ይመጣል፡፡ ፊሊስ አንዴ "ምርጥ" ተብላ ከተጠራች በኋላ ይህን እየተገነዘበችው መጥታለች፡፡ ከሁሉም የበለጠች ታላቅ ዳንሰኛ "ፕሪማ ባላሪና አሶሉታ" ተብላ ተሸለመች፡፡ ፊሊስ ለዘላለም ትታወቃለች፡፡ ከዚህ የበለጠ ምንም አትፈልግም።
ድንቅ! እንዴት ያለ አያያዝ ነው! ፊሊስ አፍቃሪ አጋርዋን አገኘች ፡፡ ስሙ ፊሊፕ ቦይድ ነበር። እሱም ሌላው ዳንሰኛ ነበር፡፡ ተጋቡ። እና በአንድ ላይ ይደንሱ ጅመር። ግማሹን ቢሆን እንጂ ከእነሱ የበለጠ የተስማማ ማንም የለም!
ፊሊስና ፊሊፕ ልጅ ባይኖራቸውም በጭራሽ አልተከፉም ነበር፡፡ ሁለቱም ሌሎች እናቶችን እና አባቶችን የሚረዱበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፡፡ ለዳንስ ልዩ ትምህርት ቤት በመክፈት "ዳንስ ለሁሉም" ሥልጠና ጀመሩ፡፡ ስለዚህ ገንዘብ የሌላቸው ልጆች በነፃ የመማር እድሉን አገኙ፡፡
አስገራሚ ስኬት እና የዳንስ ቅርስ ትታ ነበር። የእሷ ጥረት ሌሎች እውነተኛ ማንነታቸውን እንዲያገኙት ማገዝ ነው፡፡ በእሷ ጥበበኛ እግሮች የተደነቁት ተማሪዎቿ በዓለም ዙሪያ ተሰራጭተው ይገኛሉ፡፡ ሲደንሱ ከመቀመጫችን ሆነን እንመኛቸዋለን፡፡


