ስግብግቧ ሴትዮ
Alungho Rose
Abraham Muzee

ከብዙ ጊዜ በፊት፣ ካቶ የሚባል አንድ ሰው ነበር፡፡ የካቡሱ ከተማ ነዋሪ ነው፡፡ ከውሻው ጋር በአነስተኛ ቤት ውስጥ ይኖር ነበር፡፡

1

አንድ ቀን ካቶ በጠና ታመመ፡፡ የሚረዳው አንድም ሰው አልነበረም፡፡ ከህመሙ እንዳገገመም፣ በአካባቢው በቅርብ ከምትኖር ሴት ጋር ለመጋባት ወሰነ፡፡

2

በሰርጉ ሥነስርዓት ላይ እንድገኙ ዘመዶቹን እና ጓደኞቹን ጠራ፡፡ ካቶ እረዳት ያገኘሁ ስለመሰለው በጣም ተደስቶም ነበር፡፡

3

ለሙሽሪትና ለሙሽራው ብዙ ነገሮች ቀርበዋል፡፡ እነዚህም የጡብ ቅርጫት፣ ምንጣፍ፣ሙዝ፣ ለውዝ እና ሌሎች ለቤቱ የሚሆኑ ስጦታዎች ነበሩ፡፡

4

የሰርጉ ሥነስርዓት ተጠናቀቀ እና ለሰርጉ የመጡት ተጋባዦች ወደ የቤታቸው ተመለሱ፡፡ ካቶም ከሚስቱ እና ከውሻው ጋር አዲስ ኑሮ ለመጀመር ተዘጋጀ፡፡

5

በሰርጉ ማግስት፣ ካቶ ለሚስቱ ስኳር ድንች እንዲትበላ ጋበዛት፡፡ እሷ ግን ለመብላት ፈቃደኛ አልነበረችም፡፡

6

ካቶ ለአደን በሄደ ጊዜ፣ ሚስቱ ስኳር ድንቹን በሙሉ በላችው፡፡

7

ካቶ ከአደን ተመለሰ፤ እርቦት ነበር፡፡ ስኳር ድንች እንዲቀርብለት አዘዘ፡፡ ሚስቱ "ውሻው ሁሉንም በልቶታል !" አለች፡፡

8

በተከታዩ ቀን፣ ካቶ ወደ እርሻው ሄደ፡፡ ተመልሶ ሲመጣ፣ ሚስቱ ሁሉንም ሥጋ በልታው አገኘት፡፡ ለውሻው እንኳን አላቀመሰችውም፡፡

9

በሌላ ቀን፣ ካቶ ጓደኞቹን ለመጠየቅ ሄደ እና ተመልሶ ሲመጣ፣ ሚስቱ ለውዙን በሙሉ በልታዋለች፡፡ ቅርጫቱ ባዶ ሆኗል፡፡ ካቶ በአዲሷ ሚስቱ ተናደደ፡፡

10

ካቶ " በዚች ሴት ላይ አንድ ችግር አለ" ሲል አሰላሰለ፡፡ አስማት ለማድረግም ወሰነ፡፡ በአስማቱ ማሰሮ ወተት ሞላ፣ ማሰሮውን ከአልጋው ሥር አስቀመጠ እና ለማደን ወጥቶ ሄደ፡፡

11

ሴትዮዋ ማሰሮውን አየችው፣ በወተት ተሞልቷል፡፡ በአንድ ጊዜ ማሰሮውን አነሣች እና ወደ አፏ ላከችው፡፡ ወተቱን ጨልጣ ስትጠጣውም፤ ውሻው ይመለከታት ነበር፡፡

12

አለመታደል ሆነና፣ ማሰሮው በአፏ ላይ ተጣብቆ ቀረ፡፡ ማሰሮውን ለማስለቀቅ ታገለች፤ ልፋቷ ሁሉ በከንቱ ነበር፡፡ ጮኸች፤ ዘለለች፤ ፈረጠች፡፡ ማሰሮው እንደተጣበቀ ቀረ፡፡ ይህን ሁሉ ውሻው ይመለከት ነበር፡፡

13

ከዚያም ውሻው ካቶን ለመፈለግ ሮጦ ሄደ፡፡ ውሻው ጮኸ፤ ጮኸ፤ ዘለል፤ ፈረጠ፡፡ ካቶ በመሮሪያ ቤቱ አንድ ችግር እንደተፈጠረ ተገነዘበ፡፡

14

ካቶ እና ውሻው አንድ ላይ ወደ ቤት ሮጡ፡፡ ካቶ በሚስቱ አፍ ላይ ማሰሮው ተጣብቆ በማግኘቱ ተገረመ፡፡ እሷን ተመለከተ እና ተደነቀ፡፡

15

ካቶ የሚስቱን ጉንጭ ነካ ሲያድርግ፣ ማሰሮው ተላቅቆ ወደቀ፡፡ ሴትዮዋ በጣም አፈረች፡፡ ወደ ወላጆቿ ቤት ተመልሳ ለመሄድም ወሰነች፡፡

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ስግብግቧ ሴትዮ
Author - Alungho Rose, Annet Ssebaggala
Translation - Kebede Yimer
Illustration - Abraham Muzee
Language - Amharic
Level - First paragraphs