እርግማን ወይስ ምርቃን?
Alfred Esinyen
Marleen Visser

ለብዙ ወራት፣ ሰማይ ደረቅ ሆነ፡፡ ታዋቂው ዝናብ አምጪ ሎሞንጊን ለአማልእክቱ ተናገረ፡፡ ሰዎች ከሱ መኖሪያ ቤት አካባቢ ተሰብስበው፣ የተስፋውን መልእክት በጭንቀት መጠባበቅ ጀመሩ።

1

ዝናብ አምጪው ሲመጣ፣ ፈጣሪ ለሰዎቹ ቶሎ ዝናብ ሊሰጣቸው እንደሆነ አረጋገጠ፡፡ እህላቸውን መዝራት ይችላሉ፡፡

2

እኛ ዝናቡን ስንጠባበቅ ልጆች ውጭ ላይ ይጫወቱ ነበር፡፡ ከዚያ ቀን በኋላ፣ በሩቅ ምስራቅ በኩል ትላልቅ ነጫጭ ደመናዎችን አየን። እነሱ የዝናብ ደመናዎች እንደሆኑም አውቅኩ።

3

ዝናብ አምጭው ምን እንደሚል ሕዝቡ ገና እያሰላሰለ ነበር፡፡ እማዬ ጮክ ብላ "እዛ ጋ! ደመናዎቹ አሁን እየጠቆሩ ነው፡፡ ወደ ውስጥ ግቡ" አለች፡፡

4

ዝናቡ እየተንዠቀዠቀ ወረደ፡፡

5

ዝናቡን ስንጠብቅ ቆየን! መጀመሪያ ተደሰትን፡፡ ዝናቡ ግን አላባራ አለ፡፡

6

በሁሉም ቦታ ውሃ ነበር፡፡ መደራችንን ከዋናው ሰፈር የሚያገናኘው ድልድይ በጎርፍ ተወስዷል፡፡

7

ቤቶች በጎርፍ ተወሰዱ፡፡ ምን ነበር በረከቱ፣ ለእኛ ጥፋት ሆኖብናል፡፡

8

ሁሉም ሰው ለመዝራት ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ አሁን ግን መዝራት አልቻለም፡፡ የመንደሬ ሰዎች ዝናብ ሲመኙ ነበር፡፡ አሁን ግን አይፈልጉትም፡፡ የምንሻገርበት ድልድይ የለም፡፡ ብዙ ሰዎች ቤት የላቸውም፡፡

9

እናም፣ ሌላም ችግር ገጥሞናል! አዞዎች በሁሉም ቦታ ሲዋኙ አየን፡፡ ይህ ነገር ፈጽሞ ተከሥቶ አያውቅም፡፡ ግራ ገባን፡፡

10

ሁሉም ሱቆች ከወንዙ ማዶ ስለነበሩ ወደ ሱቅ መሄድ አልቻልንም፡፡ ትምህርት ቤቶችም ከወንዙ ማዶ ስለነበሩ ሕጻናት ወደ ትምህርት ቤት መሄድ አልቻሉም፡፡

11

በረከት ምን መሆን ነበረበት፣ ለእኛ እርግማን ሆነብን፡፡ ዝናብ አምጪው ሎሞንጊንም እንደኛው ተበሳጭቷል፡፡ ብቸኛው ደስተኛ ከ8 ድመቶቹ ጋር ካፑስ ነበር፡፡

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
እርግማን ወይስ ምርቃን?
Author - Alfred Esinyen
Translation - Kebede Yimer
Illustration - Marleen Visser, Natalie Propa, Silva Afonso, Vusi Malindi
Language - Amharic
Level - First paragraphs