ጅቦች ለምን ያነክሳሉ?
Oda Wako Genale
Adonay Gebru

ከበርካታ ዓመታት በፊት ጅቦች ተርበው ነበር፡፡ በድርቅ ምክንያት በተከሰተ ረሃብ ሳቢያ ፍየሎች፣ በጎችና ላሞች ሳይቀሩ ወደ ሌሎች ቦታዎች ተሰደው ነበር፡፡ ጅቦች ምንም የሚበሉት ነገር አልነበራቸውም፡፡

1

ከጅቦቹ አንዱ ‹‹በኛ ባህል ማናቸውንም የሚሰደድ ነገር እንበላለን፡፡ ተመልከቱ፤ እነዚህ ደመናዎች እየሄዱ ነው፡፡›› ጅቡ ደመናዎቹ ወደ ሌሎች ቦታዎች እየተሰደዱ መስሎታል፡፡ ‹‹እንብላቸው›› አለ፡፡

2

ወዲያውኑ ሁሉም ጅቦች ወደ ሰማይ አንጋጠው ደመናዎቹን ሲንቀሳቀሱ አዩዋቸው፡፡
አንዱ ወጣት ጅብ ‹‹ደመናዎቹን እንዴት እንደርስባቸዋለን? ከመሬት በጣም ሩቅ ናቸው›› ሲል ጠየቀ፡፡

3

ከሁሉም ጅቦች ዕድሜ-ጠገብ የሆነው ‹‹ከሁላችንም ጠንካራ የሆነው ጅብ ከታች ይቁምና ሌሎቻችን አንዳችን በሌላችን ጀርባ ላይ እንደራረብ፡፡ አንዳችን በሌላችን ጀርባ ላይ ወጥተን ደመናዎቹ ላይ እንደርሳለን›› አለ፡፡

4

ተስማምተው አንዳቸው በሌላቸው ጀርባ ላይ መውጣት ጀመሩ፡፡
በአፍታ ጊዜ ውስጥ ከጠንካራው ጅብ በስተቀር መሬት ላይ የቀረ ጅብ አልነበረም፡፡

5

የመጨረሻው ጅብ ከወጣ በኋላ መሬት ላይ ያለው ጅብ ሌሎቹ መብላት የጀመሩ መሰለው፡፡ ‹‹ከምትበሉት ምግብ ለምን ትንሽ አትሰጡኝም?›› ሲል ጠየቀ፡፡

6

ይሁን እንጂ ጅቦቹ ደመናው ላይ አልደረሱም፡፡
ምንም ምግብ ስላላገኙ መሬት ላይ ተሸክሟቸው ለቆመው ጠንካራ ጅብ የሚሰጡት ምንም ነገር አልነበራቸውም፡፡

7

ጠንካራው ጅብ መታገስ ስላቃተው ወደ ግራ ተንቀሳቀሰ፡፡ ሌሎቹ ሁሉም ወደ ግራ ወደቁ፡፡
በዚህም ምክንያት እስከ ዛሬ ድረስ ሁሉም ጅቦች የግራ እግራቸው ያነክሳል፡፡

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጅቦች ለምን ያነክሳሉ?
Author - Oda Wako Genale
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Adonay Gebru
Language - Amharic
Level - First paragraphs