

ሳራ ጀልባ አላት፡፡
ጀልባዋ ትልቅ ነው፡፡
ወንዝ ዳር ይገኛል፡፡
የተወሰኑ ሴቶች ወደ ወንዙ ይመጣሉ፡፡ አንዷ ሴትዮ በሳፋ ፍራፍሬ ይዛለች፡፡ ሌላኛዋ ዶሮ ታቅፋለች፡፡ ሌላኛዋ አንዲት ፍየል አለቻት፡፡ ሌላኛዋ ደግሞ ሁለት ፍየሎች ይዛለች፡፡
ሳራን ‹‹ወንዙን እንዴት መሻገር እንችላለን?›› በማለት ጠየቋት፡፡
ሳራም ‹‹ኑ ጀልባዬ ላይ ተሳፈሩ!›› አለቻቸው፡፡
ከዚያም የተወሰኑ ወንዶች መጡ፡፡ አንዱ ዓሣ ይዟል፡፡ ሌላኛው ብስክሌት አለችው፡፡ ሌላኛውም አንድ ጭነት በቆሎ አለው፡፡
ሌላ ሰውዬ ሁለት ጭነት በቆሎ አለው፡፡
ሳራንም ‹‹ወንዙን እንዴት መሻገር እንችላለን?›› በማለት ጠየቋት፡፡
ሳራም ‹‹ኑ ጀልባዬ ላይ ተሳፈሩ!›› አለቻቸው፡፡
የተወሰኑ እንስሳት ወደ ወንዙ መጡ፡፡ ሳራንም ‹‹ወንዙን እንዴት መሻገር እንችላለን?›› በማለት ጠየቋት፡፡
ሳራም ‹‹ኑ ጀልባዬ ላይ ተሳፈሩ!›› አለቻቸው፡፡
እንስሳቱ ጀልባዋ ላይ ተሳፈሩ፡፡
ዉሻ ጀልባዋ ላይ ተሳፈረች፡፡
ድመት ጀልባዋ ላይ ተሳፈረች፡፡
ዝንጀሮ ጀልባዋ ላይ ተሳፈረች፡፡
ጥንቸል ጀልባዋ ላይ ተሳፈረች፡፡
ኤሊ ጀልባዋ ላይ ተሳፈረች፡፡
ሚዳቋም ጀልባዋ ላይ ተሳፈረች፡፡
ዝኆን ወንዙ ጋ ደረሰ፡፡ ሳራንም ‹‹ወንዙን እንዴት መሻገር እችላለሁ?›› በማለት ጠየቃት፡፡
ሳራም ‹‹ና ጀልባዬ ላይ ተሳፈር!›› አለችው፡፡
ዝኆኑ ጀልባዋ ላይ ወጣ፡፡ ጀልባዋም በውኃ ተሞላች፡፡
...
ጀልባዋ ትንሽ ነች፡፡ በቂ ቦታ የላትም፡፡
ሳራም ‹‹ጠብቁ፣ መጀመሪያ ሴቶቹን እወስዳለሁ!›› አለች፡፡
‹‹ቀጥሎ፣ ወንዶቹን እወስዳለሁ!›› አለች ሳራ፡፡
‹‹በመጨረሻ እንስሶቹን እወስዳለሁ›› አለች ሳራ፡፡
ዝኆኑም ‹‹በቃ እኔ በእግሬ ልሂድ!›› አለ፡፡

