ውለታቢሱ ቀበሮ
Mohammed Kuyu
Jacob Kono

የራበው ቀበሮ አደን ላይ ነው፡፡

1

በአንድ ትልቅ አለት ስር አይጥ ያሳድድ ጀመር፡፡

2

የአለቱን ስር ሲቦረቡር አለቱ ተንከባሎ እግሩ ላይ ወደቀበት፡፡

3

ቀበሮው እየጮኸ ሲጣራ ጥንቸል ሰማችውና ምን እንደተከሰተ ለማየት በሩጫ ሄደች፡፡

4

ጥንቸሏ ቀበሮውን ለመርዳት ተስማማች፤ ቀበሮውም በምላሹም ራቷን ሊያበላት ቃል ገባላት፡፡

5

ጥንቸልም አለቱን በመግፋት የቀበሮውን እግር አስለቀቀችለት፡፡

6

ጥንቸልም ቃል የገባላትን እንዲሰጣት ጠየቀች፡፡ ነገር ግን የተገላቢጦሽ ሆነና ቀበሮ እበላሻለሁ ብሎ አስፈራራት፡፡

7

ከዚያም ቀበሮውና ጥንቸሏ ይዳኛቸው ዘንድ ወደ አንድ ሽማግሌ ሰውዬ ሄዱ፡፡

8

ቀበሮው ሽማግሌውን ሰውዬም እንደሚበላቸው በመዛት አስፈራራቸው፡፡

9

ሽማግሌውም፣ "እስኪ ከመወሰኔ በፊት አለቱን ልየው" አሉ፡፡

10

ቀበሮውና ጥንቸሏ ሽማግሌውን አለቱ ወዳለበት ቦታ ወሰዷቸው፡፡

11

ቀበሮው አለቱ እንዴት እግሩ ላይ ሊወድቅበት እንደቻለ አብራራ፡፡

12

ሽማግሌው ጥንቸሏን አለቱን እንዴት አድርጋ እንዳንከባለለችው ጠየቃት፡፡

13

ጥንቸሏም አለቱን አንከባልላ ቀድሞ እንደነበረው የቀበሮው እግር ላይ አደረገችው፡፡

14

ከዚያም ሽማግሌው፣ “በጄ! አሁን ጥሩ ሆነ፣ በሉ ወደቤታችን እንመለስ፡፡” አሉ፡፡

15

ሽማግሌውና ጥንቸሏ ሄዱ፡፡ ቀበሮው ግን አለቱ ተጭኖት ብቻውን ቀረ፡፡

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ውለታቢሱ ቀበሮ
Author - Mohammed Kuyu, Elizabeth Laird
Translation - Dawit Girma
Illustration - Jacob Kono
Language - Amharic
Level - First words