የባባ ውሻ
Emmaculate Rono
Heslia Schon

ይህ የባባ ውሻ ነው፡፡ ስሙ ደግሞ ቦቢ ይባላል፡፡

1

ባባ ውሻውን በጣም ይወደዋል፡፡ በየቀኑም ስጋና ዳቦ ይመግበዋል፡፡

2

ባባ ለቦቢ የሚሆን ትንሽዬ የውሻ ቤትም ሰርቶለታል፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ከመሄዱ በፊትም ቦቢ ደህና መሆኑን ሁሌ ጠዋት ጠዋት ያረጋግጣል፡፡

3

አንዳንዴ ቦቢ ወደ መኪና መንገድ እየወጣ በሚያልፉ መኪኖች ላይ “ዋው…ዋው…ዋው…” እያለ ይጮህባቸዋል፡፡

4

ቦቢ በጣም ለማዳ ውሻ ሲሆን፤ ብዙ ሰውም ይወደዋል፡፡

5

ቦቢ ከባባ ድመት ጋር መጫወት ይወዳል፡፡

6

ለቦቢ የሚሆን ቀይ ሪቫን ተገዝቶለታል፡፡ ሪቫኑም ቦቢን ቆንጆ ውሻ አድርጎታል፡፡

7

ተፈፀመ!

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የባባ ውሻ
Author - Emmaculate Rono
Translation - ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa), ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
Illustration - Heslia Schon, Wiehan de Jager, Marleen Visser, Masika Grace and Sara Saunders, Mango Tree, Silva Afonso, Vusi Malindi, José Jochicala
Language - Amharic
Level - First sentences