ሚሚ ወደ ትምህርት ቤት ሄደች
Augustine Napagi
Vusi Malindi

ሚሚ በረፍት ቀኗ ቀኑን ሙሉ ስትጫወት ዋለች፡፡

1

እናቷም ከመተኛቷ በፊት እንድትተታጠብ ነገሯት፡፡

2

የጥርስ ቡርሿንም አንስታ ጥርሷን ቦረሸች፡፡

3

እናቷም ውኃ በጎድጔዳ ሣህን አድርገው አቀረቡላት፡፡

4

ፊቷን ከታጠበችም በኃላ በፎጣ አደራረቀች፡፡

5

የመኝታ ሰዓቷ ሲደርስም ከእህቷ ጎን ሄዳ ተኛች፡፡

6

በጠዋት ተነስታም ጥርሷን ቦረሸች፣ ሰውነቷንም ተጣጠበች፡፡

7

እናቷም ልብሷን እንድትለብስ ረዷት፡፡

8

ጫማዋንም አሰረች፡፡

9

ከዚያም ወደ ትምህርት ቤት ሄደች፡፡

10

ሚሚ ወደ መማሪያ ክፍል ገብታም ትምህርቷን በጥሩ ሁኔታ ተከታተለች፡፡

11
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሚሚ ወደ ትምህርት ቤት ሄደች
Author - Augustine Napagi
Translation - ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
Illustration - Vusi Malindi
Language - Amharic
Level - First sentences