ያመለጡት እንስሳት
Cissy Kiwanuka Luyiga
Magriet Brink

አንዲት ሽማግሌ ሴትዮ ዶሮችና አንድ አሮጌ አውራ ዶሮ ነበራቸው፡፡

1

አንድ ቀን የልጅ ልጃቸው ሊጠይቃቸው መጣ፡፡ ስለሆነም አሮጌውን አውራ ዶሯቸውን ለማረድ ወሰኑ፡፡

2

አሮጌው አውራ ዶሮ ወደ አንድ ትልቅ ከተማ አመለጠ፡፡

3

አሮጌው አውራ ዶሮ ከጌቶቿ በማምለጥ ላይ የነበረችን ድመት አገኘ፡፡

4

አሮጌው አውራ ዶሮና ድመቷ በማምለጥ ላይ የነበረ ውሻ አገኙ፡፡

5

ሌላ እያመለጠ ያለ ፈረስም አገኙ፡፡

6

እንስሳቱ አንድ ቤት አገኙ፡፡ እቤቱ ውስጥም ሌቦችን አዩ!

7

ሌቦቹን ለማባረር እንስሳቱ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ዘመሩ፡፡

8

በቤቱ ውስጥ የነበረውን ምግብ በሉ፡፡

9

ሌቦቹ በኋላ ተመለሱ፡፡ እንስሶቹ አጠቋቸው፡፡

10

ሌቦቹ እስከመጨረሻው ጠፉ፡፡

11

እንስሶቹ በቤቱ ውስጥ በአንድነት በደስታ ኖሩ፡፡

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ያመለጡት እንስሳት
Author - Cissy Kiwanuka Luyiga
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Magriet Brink
Language - Amharic
Level - First words