ዋርዲት በቅሎዋ
Mesfin Habte-Mariam
Marleen Visser

አንዲት ዋርዲት የምትባል ቆንጆና ወጣት በቅሎ ነበረች፡፡

1

አንድ ሸበላ ፈረስ ‹‹ዋርዲትን ማግባት አለብኝ›› አለ፡፡

2

ፈረሱ ‹‹ነይ ወንዝ እንውረድ›› አላት፡፡

3

ፈረሱ ዋርዲትን ለትዳር ጠየቃት፡፡ ተስማማች፡፡

4

ፈረሱ ዋርዲትን ‹‹እናትና አባትሽ ግን እነማን ናቸው?›› ሲል ጠየቃት፡፡

5

ዋርዲትም ‹‹እናቴ በቤተመንግሥት ነው የምትኖረው›› ስትል መለሰች፡፡

6

‹‹እህቴ ቤተክርስቲያን ነው የምትኖተው፡፡ አታውቃትም እንዴ?››

7

‹‹ቆንጆዋ አክስቴ የመንደሩ አለቃ ንብረት ናት›› ስትል ተናገረች፡፡

8

ከዚያም አንድ አሮጌ አህያ በአቅራቢቸው አለፈ፡፡ የዋርዲት አባት ነበር፡፡

9

ዋርዲት አባቷን ሰላም አላለችውም፡፡ አላየችውምም፡፡

10

አሮጌው አህያም ‹‹ምን ሆነሽ ነው ልጄ?›› ሲል ጠየቃት፡፡

11

ፈረሱ ዋርዲትን ‹‹ይህ ደንቆሮ አህያ ማነው?›› ሲል ጠየቃት፡፡

12

ዋርዲትም ‹‹አላውቀውም›› አለች፡፡

13

ፈረሱም አህያውን በእርግጫ መታው፡፡

14

አሮጌው አህያም ስሜቱ ተነካ፡፡ ጮኸና ሞተ፡፡

15

ዋርዲት አባቷን ስለማታከብር ልጅ መውለድ አትችልም፡፡

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ዋርዲት በቅሎዋ
Author - Mesfin Habte-Mariam, Elizabeth Laird
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Marleen Visser
Language - Amharic
Level - First words