ህፃናት መጫወት ይወዳሉ
Annet Ssebaggala
Sue Kramer

ትንንሽ ህፃናት በአሻንጉሊት መጫወት ይወዳሉ፡፡

1

እኔ ገመድ ዝላይና ዥዋዥዌ መጫወት እወዳለሁ፡፡

2

ሜሪ ደግሞ ኩኩሉ መጫወት  ትወዳለች፡፡

3

አንዳንድ ልጆች ደግሞ እግር-ኳስ መጫወት ይወዳሉ፡፡

4

ሳሚ ደግሞ ሩጫ መሮጥ ይወዳል፡፡

5

አንዳንድ  ህፃናት ደግሞ ቅርጫት ኳስ
መጫወት ይወዳሉ፡፡

6

ኤልሳ እንደ እንቁራሪት ወደላይ በመዝለል መጫወት ትወዳለች፡፡

7

አንዳንዶች ደግሞ ውሃ በመረጫጨት መጫወት
ይወዳሉ፡፡

8

ሄኖክ ደግሞ ሸርተቴ መጫወት ይወዳል፡፡

9

አንዳንድ ልጆች ደግሞ የእቃቃ ባልና ሚስት ጨዋታ ይጫወታሉ፡፡

10

ሀና እና ማርታ በአሻንጉሊት መጫወት ይወዳሉ፡፡

11

እናንተስ በምን መጫወት ትወዳላችሁ?

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ህፃናት መጫወት ይወዳሉ
Author - Annet Ssebaggala
Translation - ፋሲል አሠፋ (Fasil Assefa)
Illustration - Sue Kramer, Wiehan de Jager, Mlungisi Dlamini, Angie & Upesh, Eden Daniels, Felicity Bell, Catherine Groenewald
Language - Amharic
Level - First sentences