አንዲት አዛውንት ሴትዮ ለልጅ ልጃቸው አንድ እንቁላል ሰጡት፡፡
ልጁም እንቁላሉን ለፍሬ ለቃሚዎች ሰጣቸው፡፡ እነሱም ሰበሩበት፡፡
ልጁም "አንቁላሉ የተሰጠኝ ለጥሎሽ ነበረ! እያለ አለቀሰ"
ፍራፍሬ ለቃሚዎችም በትር ሰጡት፡፡
ልጁ እንጨቱን ለግንበኞች ሰጣቸው፡፡ እነሱም ሰበሩት፡፡
ልጁ አሁንም አለቀሰ፣ "እንጨቱኮ የፍራፍሬ ለቃሚዎች ነበረ!" በማለት፡፡
ግንበኞቹም እስር ጨፌ ሰጡት፡፡
ከዚያም ልጁ አንድ እረኛ አገኘ፡፡ አንዷ ላም ሳሩን በላችበት፡፡
ልጁም አለቀሰ፡፡ “ሳሩ እኮ የግንበኞቹ ነበር!” እያለ፡፡
እረኛውም ለልጁ አንዲት ላም ሰጠው፡፡
ከዚያም ልጁ የሰርግ ድግስ ላይ ደረሰ፡፡ ከዚያም የሰርጉ ደጋሾች ላሙን አረዱበት፡፡
ልጁም አለቀሰ፣ “አዬ ጉዴ! ላሟ እኮ የእረኛው ነበረች!”
የሙሽሪት ቤተሰቦችም ሙሽሪትን ለልጁ አጋቡት፡፡