

ከረጅም ጊዜ በፊት መብራቴና ከተማ ምግብ በመጋራት ይኖሩ ነበር፡፡
መብራቴ ‹‹አብረን መብላታቸን ካልቀረ አብረን እንቆፍር›› አለ፡፡
መብራቴ ለከተማ ‹‹አንተ ትቆፍራለህ እኔ እተክላለሁ›› አለ፡፡
መብራቴ ለከተማ ‹‹አንተ ትተክላለህ፣ እኔ አርማለሁ›› አለው፡፡
የዘንጋዳው እሸት ሲደርስ ከተማ ለመብራቴ እንቁረጠው የሚል ሃሳብ አመጣለት፡፡
መብራቴም ‹‹አንተ ትቆርጣለህ፤ እኔ ጎተራው ውስጥ እጨምራለሁ›› አለው፡፡
መብራቴ ሰነፍ ነበር፡፡ ስለዚህ ከተማ የዘንጋዳውን ዘለላ ብቻ ሰጠው፡፡
መብራቴ የዘንጋዳውን ጣት ብቻ ወሰደ፡፡ ከዚያም ዶሮን አገኛት፡፡
ዶሮም ዘንጋዳውን በላች፡፡
ለመብራቴም እንቁላል ሰጠችው፡፡
መብራቴ የተወሰኑ ልጆችን አገኘ፡፡
እንቁላሉንም ሰበሩበት፡፡
ልጆቹ ለመብራቴ ማንጎ ሰጡት፡፡
መብራቴ በቀቀንን አገኛት፡፡ በቀቀን ማንጎውን በልታ ላባ ሰጠችው፡፡
ሐይቅ ላባውን ወስዶ ለመብራቴ ትንሽ ውኃ ሰጠው፡፡
መብራቴ ውኃውን የከሰል አክሳይ እሳት ለማጥፋት ተጠቀመበት፡፡
ባለከሰሉ አንጥረኛ ለመብራቴ መጥረቢያ ሰጠው፡፡
መብራቴ ባለ ሥጋ ቤቶችን አገኘ፡፡ መጥረቢያውን ሰበሩበት፡፡
መብራቴ የበሬውን ራስና ጭራ ወሰደ፡፡
መብራቴ ያደረገውን እዩ!
ከዚያም ‹‹የንጉሡ በሬ ጭቃ ውስጥ ተቀረቀረ›› እያለ ጮኸ፡፡
ሰዎች ሊረዱት መጡ፡፡ ‹‹ጭራውንና ራሱን ሳቡ›› አላቸው መብራቴ፡፡
‹‹ከብቶቻችሁን ለንጉሡ እንድሰጥ ስጡኝ›› አላቸው መብራቴ፡፡

