ጴጥሮስና ውሻው
Bethelihem Waltenegus
Brian Wambi

ከእለታት አንድ ቀን ጴጥሮስ የሚባል ልጅ ነበር፡፡ በጣም ጎበዝ ተማሪ ነበር፡፡ ከክፍል አንደኛ ስለሚወጣ ወላጆቹ ይኮሩበት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ጴጥሮስ የሚያጫውተው ወንድም፣ እህት፣ ወይም የቤት እንስሳ እንዲኖረው ይመኝ ነበር፡፡

1

አንድ ቀን እናቱን እንዲህ ሲል ጠየቃት ‹‹ውጪ ልጫወት?›› ‹‹ሳጠና ስላረፈድኩ አሁን ከጓደኞቼ ጋር ለመጫወት እፈልጋሁ›› በማለት ሃሳብ አቀረበ፡፡

2

ወደ መጫወቻ ሜዳው በመሄድም ላይ ሳለ ጴጥሮስ አንድ ያልተለመደ ነገር አየ፡፡ ነጭና ቡናማ መልክ ያለው ቡችላ ነበር፡፡ ቡችላው ጉድጓድ ውስጥ ተቀርቅሮ ፈርቶ ነበር፡፡ ‹‹አይዞህ፤ አልጎዳህም፡፡ እንዲያውም እረዳሃለሁ›› አለው ጴጥሮስ፡፡

3

ጴጥሮስ ቡችላውን ከጉድጓዱ ውስጥ አወጣው፡፡ ቡችላውም በደስታ እየጮኸ በልጁ ዙሪያ ይጮህና የልጁን እግር ይልስ ጀመር፡፡ ወደ ጨዋታው ሜዳ እየሄዱ ሳለ ‹‹የኔ ዉሻ ትሆናለህ›› አለው ጴጥሮስ በመደሰት፡፡

4

ቡችላውም ልጁን ቀድሞት ሮጠ፡፡ የጴጥሮስ ጓደኞች ቡችላው ወደነሱ ሲሮጥ ሲያዩት ‹‹ይህ ቡችላ አደገኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ሊነክሰን ይችላል›› አሉ፡፡ ድንጋይ አንስተው ወረወሩበት፡፡ ጴጥሮስ እየሮጠ ጓደኞቹ እንዲያቆሙ ይጮህ ጀመር፡፡

5

ጓደኞቹ ጴጥሮስን አልሰሙትም፡፡ ቡችላው ህይወቱን ለማትረፍ በተቻለው መጠን በፍጥነት ሮጠ፡፡ ከዚያም ከሚያሳድዱት ልጆች ተደበቀ፡፡ አላገኙትም፡፡

6

የጴጥሮስ ጓደኞች ወደ ሜዳው ሲመለሱ ጴጥሮስን ሲያለቅስ አገኙት፡፡ ‹‹ምን ሆነህ ነው?›› ሲል ከልጆቹ አንዱ ጠየቀው፡፡ ‹‹ዉሻዬን አሳደዳችሁብኛ›› በማለት ጴጥሮስ አለቀሰ፡፡ ልጆቹም ተደናግጠው ‹‹ያንተ ዉሻ መሆኑን አላወቅንም እኮ፡፡ እናዝናለን፡፡ ና እንፈልገው›› አሉት፡፡

7

‹‹ምን ዋጋ አለው? ውሻየን ልናገኘው አንችልም›› አላቸው ጴጥሮስ በሚያሳዝን ድምጽ፡፡ ‹‹አይ እናገኘዋለን፡፡ ተነስ ጴጥሮስ፣ ቡችላህን እናገኘዋን፡፡ ተስፋ መቁረጥ አይገባንም›› አሉት ጓደኞቹ በማጽናናት ድምጽ፡፡

8

ጴጥሮስና ጓደኞቹ ውሻውን ከሰዓት በኋላ ሙሉውን እስኪደክማቸው ድረስ ፈለጉት፡፡ ‹‹አንድ ውሻውን ላገኝ የምችልበት ቦታ አለ፡፡ እዚያ ካላገኘነው ፍለጋዬን አቆማለሁ፡፡ ኑ! ወደ ወንዙ እንሂድ›› አላቸው ጴጥሮስ መጨረሻ፡፡

9

ቡችላው ልጆቹ ሲመጡ ሲያያቸው ፈራ፡፡ ወንዙን ለማቋረጥ ቢሞክርም ውሃውን ፈራ፡፡ ሊዘል ሲል ጴጥሮስ ‹‹ቁም! አትዝለል!›› ሲል ሰማው፡፡

10

ቡችላው ዘወር ሲል ጴጥሮስን አየውና ወደሱ ሮጠ፡፡ ጴጥሮስም ቡችላውን አቀፈው፤ ቡችላው በበኩሉ የጴጥሮስን ፊት ላስ ላስ አደረገ፡፡ ‹‹ጓደኛዬ! እስከመጨረሻው ሄደሃል ብዬ አስቤ ነበር!›› በማለት ጴጥሮስ አለቀሰ፡፡

11

ከመጫወቻው ሜዳም እንደደረሱ ጴጥሮስ ጓደኞቹን ትንሽ መከራቸው፡፡ ‹‹አንድን ውሳኔ ከመወሰናችሁ በፊት፣ የሚያስከትለውን ነገር አስቡ፡፡ ሌሎቹን እንዳትጎዱ ተጠንቀቁ፡፡›› ጓደኞቹም ስለተናገረው ነገር አሰቡና ‹‹ይቅርታ፡፡ ቡችላው የኛም ጓደኛ ይሆናል›› አሉት፡፡

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጴጥሮስና ውሻው
Author - Bethelihem Waltenegus
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Brian Wambi
Language - Amharic
Level - First paragraphs