የእንቁራሪት ቆዳ
Alice Mulwa
Rob Owen

ሞድ የተባለው እንቁራሪት ውኃ ውስጥ መኖር ሰለቸው፡፡

1

‹‹ተጠንቀቅ›› አለ ኤሊ፡፡ ‹‹ቆዳህ ይደርቃል እኮ፡፡››

2

ሞድ ግን አዲስ ነገር ለማየት ስለፈለገ ዘሎ ወጣ፡፡

3

ዙሪያ ገባውን ቃኘ፡፡

4

አንድ ኩሬ ስር ወይንጠጅ እስስት አገኘ፡፡

5

እስስቷ ወደ ሮዝነት መቀየር ጀመረች! ሞድ ዘሎ ጠፋ፡፡

6

ከዚያ ጅብ እሳት ሲያይዝ አየው፡፡

7

እሳቱ ወደ ሞድ ተቃረበ፡፡

8

እሳቱ ቆዳውን አቃጠለው፡፡ ሞድ ተመልሶ ወደ ኩሬው ገባ፡፡

9

ቆዳው ግን ቆሳሰለ፡፡

10

ሞድ ከአንድ አለት ስር መኖሪያ አገኘ፡፡ ቆዳውም ደረቀ፤ ጠነከረ፡፡

11

አሁን እንቁራሪት ብቻ ነው ለስላሳ ቆዳ ያለውና በውኃ አቅራቢያ የሚኖረው፡፡

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የእንቁራሪት ቆዳ
Author - Alice Mulwa
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Rob Owen
Language - Amharic
Level - First words