ጦጣና አዞ
Mulualem Daba
Abraham Muzee

ጦጢት አዞውን ሐይቅ ዳር አገኘችው፡፡

1

‹‹የት ነው የምትኖረው?›› ስትል ጦጢት ጠየቀችው፡፡ ‹‹ሐይቁ ውስጥ›› አላት አዞው፡

2

‹‹አንቺስ የት ነው የምትኖሪው?›› አላት አዞው፡፡ ‹‹ዛፍ ላይ›› ስትል መለሰች ጦጣዋ፡፡

3

‹‹መዋኘት ትችያለሽ?›› ሲል ጠየቃት አዞው፡፡

4

‹‹መዋኘት አልችልም››አለች ጦጢት፡፡ ‹‹አስተምርሻለኋ፡፡››

5

‹‹ጓደኞች አይደለን እንዴ? አትፍሪ›› አላት አዞው፡፡

6

‹‹ጦጢት፣ አጎቴ አሞታል፡፡ ሥጋ ይፈልጋል›› አላት አዞው፡፡

7

ጦጢት በጣም ፈርታለች፡፡ አዞው ይበላት ይሆን?

8

ጦጢት ከአዞው ለማምለጥ ፈልጋለች፡፡

9

ጦጢት አንድ ሐሳብ መጣላት፡፡

10

‹‹ለአጎትህ ልቤን እሰጥህና ትወስድለታለህ›› በማለት ለአዞው ቃል ገባችለት፡፡

11

‹‹ልቤ መሬቱን አልፎ ያለው ዛፍ ላይ ነው›› አለችው፡፡

12

‹‹ልብሽን ታመጭዋለሽ?›› ሲል ጠየቃት አዞው፡፡ ‹‹አዎን›› አለችው፡፡

13

አዞውም ወደ መሬቱ እየዋኘ መለሳት፡፡ ጦጢትም ወደ ዛፉ ሮጠች፡፡

14

‹‹ጓደኛዬ አይደለሽም፤ ዋሽተሸኛል!›› አላት አዞው፡፡

15

‹‹በቃ በቃ! ጓደኛማቾች አይደለንም፤ ልትበላኝ ትፈልጋለህ›› አለችው ጢጢትም መልሳ፡፡

16
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጦጣና አዞ
Author - Mulualem Daba
Translation - Mezemir Girma
Illustration - Abraham Muzee
Language - Amharic
Level - First words