ጆጆና ላሚቷ
Isiira Patrick
Rob Owen

ጆጆ ትንሽ ልጅ ነዉ።

1

ጆጆ የሚኖረው ከእናቱ እና ከአንዲት ላም ጋር ነዉ።

2

ጆጆ ላሚቷን በጣም ይወዳታል።

3

ሁልጊዜ ጠዋት ጠዋትም የጆጆ እናት ላሚቷን ያልቧት ነበር።

4

ጆጆም ወተት በደንብ ይጠጣል።

5

ጆጆ ላሚቷን ወደ ግጦሽ ይወስዳታል።

6

ውሀም ከጉድጓድ እየቀዳ ያጠጣታል።

7

የጆጆ እናትም ማድ ቤት ውስጥ ምግብ ያበስላሉ።

8

ጆጆም ምግብ በደንብ ይመገባል።

9

ጆጆ እግር ኳስ ከጓደኛው ጋር ይጫወታል።

10

ጆጆ መጻሕፍትን ማንበብ ይወዳል።

11

ጆጆ ላሚቷን ተሰናብቶ ወደ መኝታው ሄደ።

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጆጆና ላሚቷ
Author - Isiira Patrick
Translation - ፋሲል አሰፋ (Fasil Assefa)
Illustration - Rob Owen, Catherine Groenewald
Language - Amharic
Level - First sentences