

እሳት፣ ውሃ፣ እውነትና ውሸት ጓደኛሞች ነበሩ፡፡
ውሸት ግን ደስተኛ ስላልነበር ጓደኝነቱን ለማፍረስ ፈለገ፡፡
ውሸት አንድ ቀን እንዲህ አለ፡፡ ''ለምን ሁላችንም መሬት ፍለጋ አንሰማራም? ከዚያም እያንዳንዳችን ግዛት ይኖረናል፡፡'' በዚህ ሁሉም ተስማምተው ጉዞ ጀመሩ፡፡
ውሸት ወደ ውሃ ሄዶ እንዲህ አለው፡፡ ''እሳት ክፉ ጠላታችን ነው፡፡ ሁሉንም ያቃጥላል፡፡ እሱ የማይኖርበት ግዛት መፈለግ አለብን፡፡''
ውሃም ''ታዲያ ምን እናድርግ?'' ሲል ጠየቀ፡፡ ውሸትም ''እውነትን ልንገድላት ይገባል፡፡ እሱን ለመግደል ብቸኛው ኃይል ያለህ አንተ ነህ፡፡ ልትቀመጥ ስትል ውሃ ድፋባትና አጥፋት!'' ሲል መለሰ፡፡
ውሃ ደግሞ ''ያንን ካደረግኩማ መሬት ላይ ፈስሼ ተመልሼ መምጣት አልችልም'' አለ፡፡ ውሸት ግን ''ችግር የለም የተወሰኑ ድንጋዮች አነጥፍልሃለሁ፡፡ ስለዚህ አትጠፋም፡፡ መልሼ ደግሞ እሰበስብሃለሁ'' አለ፡፡ ውሸት ድንጋዮቹን አነጠፈ፡፡
ያልጠረጠረው እሳት እንደተቀመጠ ውሃ ተደፋበት፡፡ በዚህም መንገድ ውሸት እሳትን አጥፍቶ መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ውሸት ለውሃ ''እይ፣ ለምን በዚህ ተራራ ላይ ተቀምጠህ አገር አታይም?'' ይለዋል፡፡
ውሃ እንደተቀመጠ ውሸት ሹልክ ብሎ ሄዶ ከስሩ ያሉትን ድንጋዮች ይፈነቅልበታል፡፡ በመሆኑም ውሃ ፈሰሰና አለቀ፤ ጠፋ፡፡
አሁን ውሸት እውነትን ማጥፋት ያስፈልገዋል፡፡ አንድ ትልቅ ተራራ ጋ ሲደርሱ ውሸት ለእውነት ከተራራው ጥግ እንዲጠብቀው ይነግረዋል፡፡
እውነትን ለመጨፍለቅ ትልቅ ድንጋይ አነሳ፡፡
ድንጋዩ ሲሰበር አልማዝ፣ ወርቅና የተለያዩ ውድ ዋጋ ያላቸው ነገሮች ተዘረገፉ፡፡ እውነትም ከተሰባበረው ድንጋይ ውስጥ መውጣት ቻለ፡፡
ውሸት የእውነትን መጨረሻ ለማየት ወጣ፡፡ ሁሉንም ውድ ነገሮችም አየ፡፡ ''እነዚህ ሁሉ ከየት መጡ?'' ሲል ጠየቀው፡፡
''ድንጋዩ ሲያርፍብኝ የወጣው ይህ ነው'' አለው እውነት፡፡ ውሸትም እነዚህን ውድ ነገሮች ለማግኘት ተመኘ፡፡ ''ወደ ተራራው ጥግ እሄዳለሁ፡፡ ሂድና አንድ ሌላ ድንጋይ ወርውርብኝ'' አለው፡፡.
በዚህም መሰረት እውነት ወደ ላይ ወጣና ትልቅ ድንጋይ ወረወረበት፡፡
ድንጋዩም በውሸት ራስ ላይ አርፎ ገደለው፡፡

