የአባት ውርስ
Lemu Wachile
Jacob Kono

በድሮ ጊዜ ሁለት ታታሪ ባልና ሚስት ገበሬዎች ነበሩ፡፡ ሁለት ልጆችም ነበሯቸው፡፡

1

ባልና ሚስቱ ጠንክረው ስለሚሰሩ ሀብታሞች ነበሩ፡፡ ልጆቻቸውም ጥሩ ሕይወት እንዲኖሩላቸው ይፈልጉ ነበር፡፡ ልጆቻቸውንም ምንም ዓይነት ስራ አያሰሯቸውም ነበር፡፡

2

ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን ሚስትዮዋ ሞተች፡፡

3

አሁንም ባልየው ልጆቹ ስራ እንዲሰሩ አልፈለገም፡፡ የውጪውንም ሆነ የቤት ውስጡን ስራ የሚሰራው እሱው ነበር፡፡

4

ጊዜው እየገፋ ሲሄድ ግን አባትዬው አረጀ፡፡ ታመመ፡፡ ከሞተም በኋላ ልጆቹ ምን እንደሚበጃቸው ይጨነቅ ጀመር፡፡ ራሳቸውን አይችሉልኝም በማለት ሃሳብ ገባው፡፡

5

ልጆቹንም ጠራቸውና ''የማወርሳችሁ በማሳው ላይ የተቀበረ ወርቅ አለ፡፡ ቆፍራችሁ አግኙት'' አላቸው፡፡

6

ጎረቤቶቹንም ጠርቶ ''እንግዲህ መሞቴ ነው፤ ልጆቼም ረዳት-አልባ ናቸው፡፡ ራሳቸውን መቻልን እስኪያውቁ ድረስ አግዙልኝ'' አላቸው፡፡

7

ሰውየውም ከሞተ በኋላ ሰዎቹ ለልጆቹ ለተወሰነ ጊዜ ምግብ ሰጧቸው፡፡

8

ወንድማማቾቹም ወርቃቸውን ሌላ ሰው እንዳይወስድባቸው በመፍራት ራሳቸው ማሳውን ለመቆፈር ወሰኑ፡፡

9

ማሳውን ሙሉ በሙሉ ቢቆፍሩም ወርቅ ግን ሊያገኙ አልቻሉም፡፡

10

ቁጭ ብለው ሳለ አንደኛው ልጅ ሌላኛውን ''አባታችን አታሎናል ማለት ነው እንዴ?'' በማለት ጠየቀው፡፡ ሌላኛውም ''አይ፣ አባታችን እርሻ ወርቅ መሆኑን ሊያስተምረን ፈልጎ ነው፡፡ ማሳውን ቆፍረንና አርሰን ከዘራነው እንበለጽጋለን'' በማለት መለሰለት፡፡

11

በመሆኑም መሬቱን ቆፍረው ዘር ዘሩበት፡፡ ስንዴ አምርተውም በእጅጉ በለጸጉ፡፡

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የአባት ውርስ
Author - Lemu Wachile, Elizabeth Laird
Translation - መዘምር ግርማ
Illustration - Jacob Kono
Language - Amharic
Level - First paragraphs