ነብርና ሚዳቋ
Magabi Enyew Gessesse
Isaac Okwir

ነብር ሚዳቋን ለመያዝ ሁልጊዜ ትጥር ነበር፡፡

1

ሚዳቋም ሁሌ ታመልጣት ነበር፡፡

2

አንድ ቀን ነብር ሚዳቋን ጠርታ ''ጓደኛ እንሁን፡፡ አንቺ የምትበይውን እኔ አልበላ፡፡ ምን ያጣላናል?'' አለቻት፡፡

3

ሚዳቋም በሃሳቡ ተስማማች፡፡ ነብርም ''ጓደኞች ለመሆን ቃል እንገባባ፡፡ አንዳችን ቃለ-መሐላውን ካፈረስን፤ ልጅ ይንሳን'' አለች፡፡

4

ጓደኞች ለመሆን ቃል ተገባቡ፡፡ ማታ ሚዳቋ ዛፍ ስር ተኝታለች፡፡ ነብር ደግሞ ከበላይዋ በዛፉ ቅርንጫፍ ላይ ተኝታለች፡፡

5

ሚዳቋዋ ቶሎ ወፈረች፡፡ ነብሯ ግን ከሳች፡፡

6

ነብሯ ወፍራም ሚዳቋ መብላት አማራት፡፡ ለራሷም ''ስለ ቃለ-መሐላው ግድም አይሰጠኝ፡፡ ልጅ የለኝ እኔ! ምን ቸገረኝ!'' አለች፡፡

7

ሚዳቋዋን ለመያዝ ነብሯ ዘለለች፡፡ ስትዘል ግን በሁለት የዛፍ ቅርንጫፎች መሃል ተጣበቀች፡፡

8

ሚዳቋዋም ደነገጠች፡፡ ተስፈንጥራ ''ባ! ባ!'' ብላ ጮኸች፡፡

9

ነብሯ ''ወዳጄ፣ እርጂኝ፡፡ የጓደኝነት ቃሉን ያፈረሰ ልጅ ይንሳው ተባብለናል'' ስትል ለመነቻት፡፡

10

ሚዳቋዋም ''አባትሽም ይህን ቃል ገብቶ ይሆናል፡፡ አሁን ይኸው ባንቺ ደረሰብሽ'' ስትል መለሰችላት፡፡

11
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ነብርና ሚዳቋ
Author - Magabi Enyew Gessesse, Elizabeth Laird
Translation - መዘምር ግርማ
Illustration - Isaac Okwir
Language - Amharic
Level - First sentences