ፋንቱና እቅዷ
Mary Jaffer

ፋንቱ በድሉ እባላለሁ። የአንደኛ ክፍል ተማሪ ነኝ። ዕድሜዬ ሰባት ዓመት ነው። ጥሩ ልጅና ጎበዝ ተማሪ መሆን እፈልጋለሁ።

1

በጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ ወደ መጸዳጃ ቤት እሄዳለሁ።

2

እጄንና ፊቴን እታጠባለሁ፤ አፌን በደንብ እጉመጠመጣለሁ።

3

ቁርሴን በልቼ ስጨርስ ደብተሮቼንና መጻሕፍቴን ይዤ ወደ ትምህርት ቤት እሄዳለሁ።

4

በመንገድ ላይ አልጫወትም፤ የመኪና መንገድ ሳቋርጥም እጠነቀቃለሁ።

5

በትምህርት ቤቴ በሰዓቱ እገኛለሁ።

6

ለሰንደቅ አላማ መዝሙር እሰለፋለሁ።

7

ክፍል ገብቼ ስሜ ሲጠራ ቆሜ ''አቤት'' እላለሁ።

8

መምህሬ ሲያስረዱ በጥንቃቄ አዳምጣለሁ፤ ያልገባኝንም እጠይቃለሁ።

9

መምህሬ በጥቁር ሰሌዳ ላይ የጻፉትን በደብተሮቼ ላይ እገለብጣለሁ።

10

ከጓደኞቼ ጋር በቡድን አጠናለሁ።

11

የክፍልና የቤት ሥራዬን ቀድሜ አሳርማለሁ።

12

በእረፍት ጊዜና በምሳ ሰዓት ከጓደኞቼ ጋር እጫወታለሁ።

13

ከጓደኞቼ ጋር በፍጹም አልጣላም፤ ካጠፋሁም ይቅርታ እጠይቃለሁ።

14

በኔ ጉዳይ ላይ መምህሬና ወላጆቼ በቅርብ ይወያያሉ።

15

እኔም የሁሉንም ምክር በአክብሮት እቀበላለሁ።

16

ከትምህርት በኋላ ትንሽ ተጫውቼ አጠናለሁ፤ የቤት ሥራዬንም እሠራለሁ።

17

እጄን ታጥቤ እራቴን ከበላሁ በኋላ አፌን ተጉመጥምጬ እተኛለሁ።

18
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ፋንቱና እቅዷ
Author - Mary Jaffer
Translation - ነጋሳ እጀታ (Negassa Ejeta)
Illustration -
Language - Amharic
Level - First sentences