የኔ መንደር
Wendy Parry
Wiehan de Jager

በኢትዮጵያ ውስጥ ቦሌ በምትባል መንደር እኖራለሁ፡፡ መንደሬ በጣም ቆንጆ ነች፡፡

1

በመንደሩ የሚኖሩት ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ይወዳሉ፡፡ ''አስተማሪዎቻችንን እንወዳቸዋለን፡፡''

2

በትምህርት ቤታችን ማንበብ እንወዳለን፡፡ ቁጥር መቁጠር እንወዳለን፡፡ 1 2 3 4 5

3

ከጓደኞቻችን ጋር መጫወት ደስ ይለናል፡፡ ኳስ እየለጋን መጫወት ደስ ይለናል፡፡

4

በመንደራችን ውስጥ ሙዝ መብላት ደስ ይለናል፡፡

5

አሳማዎችን ማባረር እንወዳለን፡፡

6

ከጓደኞቻችን ጋር መጫወት ደስ ይለናል፡

7
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የኔ መንደር
Author - Wendy Parry
Translation - Misraq Wondale, መዘምር ግርማ
Illustration - Wiehan de Jager, Mario Kart, Laura Libertore, Vusi Malindi, Catherine Groenewald
Language - Amharic
Level - First sentences