

በጥንት ጊዜ ልጅ እንዲኖራቸው አጥብቀው ይፈልጉ የነበሩ አንዲት አሮጊት ሴትዮ ይኖሩ ነበር፡፡
ሴትዮዋ ምርጥ የሸክላ አፈር አምጥተው ሴት ልጅ ያበጁ ጀመር፡፡
ከጭቃ የተሰራችው ሴት ልጅ ወደ እውነተኛ ልጅነት ተቀየረች፡፡
አሮጊቷ ሴትዮ በጣም ተደሰቱ፡፡ ልጂቷን አስካለ ብለው ስም አወጡላት፡፡ ሴትዮዋ አስካለን በጣም ወደዷት፡፡
አስካለን እናቷ ከቤት እንዳትወጣ ቢያስጠነቅቋትም አልሰማ አለች፡፡ እናትዬዋ ሳያውቁ አስካለ ቀስ ብላ ከቤት ወጥታ ከሌሎች ህጻናት ጋር ለመጫወት ትሄዳለች፡፡
አንድ ቀን አስካለ ከሌሎች ልጆች ጋር ልትጫወት እንደወጣች ሃይለኛ ዝናብ መዝነብ ጀመረ፡፡
ሌሎቹ ልጆች ወደየቤቶቻቸው ሮጡ፤ አስካለ ግን ወደቤቷ እየሮጠች እያለ እግሯ ተሰበረ፡፡ ኩርምት ብላ ከቁጥቋጦዎች መሃል ተቀመጠች፡፡
ሌሎቹ ህጻናት ለወላጆቻቸው አስካለን ምን እንዳጋጠማት ተናገሩ፡፡ በጣም አዝነውና ተደናግጠው ነበር፡፡
አሮጊቷ ሴትዮ በብቸኛዋ ልጃቸው ላይ ምን እንደደረሰ በሰሙ ጊዜ ለብዙ ቀናት አለቀሱ፡፡ ከዚያም አሮጊቷን ሊያጽናኑ የሄዱ የመንደሩ ሰዎች አስካለን ልትተካ የምትችል ትንሽዬ ልጅ ጉዲፈቻ ሊያመጡላቸው ወሰኑ፡፡
ይሄ ግን አስፈላጊ አልነበረም፡፡ ትልቅ አስደናቂ ገጸ- በረከት ለአሮጊቷ ሴትዮ!
ጉዲፈቻዋ ልጅ ወደ አሮጊቷ ዘንድ ከመጣች ከጥቂት ቀናት በኋላ ቤቱ በቀስታ ተንኳኳ፡፡
''ማን ሊሆን ይችላል?'' አሉ አሮጊቷ በመደነቅ፡፡ በሩን ከፍተው ሲመለከቱ፤ ያዩትን ነገር ማመን አልቻሉም፡፡.
አስካለ ወደ ቤቷ ተመልሳ ነበር፡፡ ነገር ግን ደካክማና አሟትም ነበር፡፡
የአስካለ እናት ያላቸውን ንብረት በሙሉ ሸጡ፡፡ ገብዘባቸውንም አስካለን ለማሳከም አዋሉት፡፡ አስካለ የሰፈሩ በጣም ቆንጅዬ ልጅ ሆና አደገች፡፡

