የአይጢት ቤት
Michele Fry
Amy Uzzell

አይጧ አዲስ ቤት እየፈለገች ነው፡፡

1

ይሄ ቤት ጥሩ ይመስላል፡፡

2

''መጥተሽ ከእኔ ጋር መተኛት ትችያለሽ'' አላት አንድ ቡችላ፡፡ ''አመሰግናለሁ'' አለች አይጥ፡፡.

3

በዚያ ሌሊት አይጧ ደስ የማይል ነገር በህልሟ እየመጣ ስትረበሽ አደረች፡፡

4

''መጥተሽ ከእኔ ጋር መተኛት ትችያለሽ''  አለቻት በቀቀን፡፡ ''አመሰግናለሁ'' አለች አይጥ፡፡.

5

በዚያ ሌሊት አይጧ ጫጫታ የበዛበትና አስፈሪ ህልም ስታይ አደረች፡፡

6

''መጥተሽ ከእኔ ጋር መተኛት ትችያለሽ'' አላት ዓሣ፡፡ ''አመሰግናለሁ'' አለች አይጥ፡፡.

7

በዚያ ሌሊት አይጧ ያየችው ህልም ቀዝቃዛና ርጥበታማ ነበር፡፡

8

አይጧ ሞቃትና ደረቅ የሆነ ቦታ ፈለገች፡፡

9

10

ከዚያም በአቅራቢያዋ የመጽሐፍ መደርደሪያ አገኘች፡፡

11

በዚያ ሌሊት አይጧ ሞቃትና ደስ የሚል ህልም አየች፡፡ መልካም እንቅልፍ፣ አይጢት!

12
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የአይጢት ቤት
Author - Michele Fry
Translation - ዳዊት ግርማ, መዘምር ግርማ
Illustration - Amy Uzzell
Language - Amharic
Level - First paragraphs