አዋቂው ሰውዬ
Cornelius Wekunya
Joshua Waswa

ከዕለታት አንድ ቀን ወጣቶች ከታላላቆቻቸው ይበልጥ አዋቂ ናቸው ብሎ የሚያስብ ሰውዬ ነበር፡፡ ይህ ሰውዬ ለባለቤቱ ''እኔ ወጣት ነኝ፤ ከታላቆቼ ሁሉ ይበልጥ አዋቂ ነኝ'' አላት፡፡  ባለቤቱ ደግሞ ''አንተ ከአባቴ በላይ አዋቂ አይደለህም!'' አለችው፡፡

1

አንድ ቀን የሰውዬው ባለቤት ወላጆቿን ለማየት ትሄዳለች፡፡ ከዛም ባሏ ያለውን ነገር ለአባቷ ትናገራለች። ከዚያም አባቷ ''በዪ ልጄ አሁን ሄደሽ 'ካንተና ከአባቴ ማነው አዋቂ?' ብለሽ ጠይቂው'' አሏት፡፡

2

የሰውዬው ባለቤት አባቷ ያሏትን ነገር ሄዳ ለባለቤቷ ትነግረዋለች። ባለቤቷም ''ሄደሽ አባትሽን 'ከጭጋግ ጠላ ያዘጋጁልኝ' ብሎዎታል በያቸው'' ብሎ ይልካታል። ''አሁን በጣም አዋቂ ሰው እንደሆንኩ አማቴ ይረዳሉ'' አለና ሳቅ አለ። ማንም ከጭጋግ ጠላ መስራት አይችልም።

3

እሷም መልዕክቱን ለማድረስ ወደ አባቷ ሄዳ ነገረቻቸው። አባትየው በጣም ሳቁ፡፡ ምክንያቱም ምንም አይነት ጠላ ከጭጋግ አይሰራም። አባቷም ''በዪ ልጄ፣ አሁን ሄደሽ 'እሺ ከጭጋግ ጠላ አዘጋጅልሃለሁ፤ ነገር ግን ጠላውን የሚወስደው ወንድም ሴትም መሆን የለበትም' በዪው'' ይሏታል።

4

ይህን መልዕክት ሄዳ ለባለቤቷ ስትነግረው ባለቤቷ በመልሱ ተገረመና '''ልጅ ይሮጣል እንጂ አባቱን አይቀድምም' የሚባለው ነገር ለካ እውነት ነው'' አለ፡፡

5
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አዋቂው ሰውዬ
Author - Cornelius Wekunya
Translation - ከድር ኢብራሂም, ፋሲካ ምንዳ
Illustration - Joshua Waswa
Language - Amharic
Level - First paragraphs