ቼዝ እና የቤተሰብ ድርሻ
Jamie Luketa
Jamie Luketa

አንድ ሮድኒ የሚባል ከቤተሰቡ ጋር የሚኖር ልጅ ነበር።
እናቱ ጃሚማ፣ አባቱ ደግሞ ማይክ ይባላሉ።
ሱዚ እና ሎላ የሚባሉ እህቶች አሉት።
ሮድኒ ለቤቱ ታናሽ ልጅ ነዉ።

1

ሮድኒ ቼዝ መጫወት ይወዳል።
ቼዝ መጫወት በጣም ስለሚወድ፣ ሲጫወት ምንም አያወራም።

2

አንድ ቀን ሮድኒ ትምህርት ቤት ቼዝ እየተጫወተ እያለ፣ ጨዋታዉ ስለቤተሰብ ሊሆን እንደሚችል አሰበ።

3

ማይክ ንጉስ ነዉ። ጃሚማ ንግስት ነች፣ ለዚህም ነዉ ስልጣን ያላት።
ሱዚ እና ሎላ ጦረኞች እና ጳጳሳት ናቸው።
ሮድኒ ታናሹ ልጅ ስለሆነ፣ ወታደር ነው።

4

ሮድኒ ይህንን ካሰበ በኃላ፣ ለቤተሰቡ ለመንገር ወደቤት ሮጠ።

5

መጀመሪያ ቤተሰቡ ሁሉ ሳቁ፣ ከዛ በኃላ ግን ገባቸዉ።
ሮድኒ የቤተሰቡን ድርሻና ለምን እሱ ወታደር እንደሆነ አስረዳቸዉ።

6

ሮድኒ እናቱ ንግስት እንደሆነች ፣ አባቱ ደግሞ ንጉስ እንደሆነ ነገራቸዉ።
እህቶቹ ደግሞ ጦረኞች እና ጳጳሳት እንደሆኑ ነገራቸዉ።

7

ሮድኒ ወታደር የሆነዉ ጀብድ ስለሚወድ ነዉ።
አንዳንድ መስዋዕትነት ቢያስከፍለዉም ፣ የሚፈልገዉን ነገር መሆን ይችላል።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ቼዝ እና የቤተሰብ ድርሻ
Author - Jamie Luketa
Adaptation - Fikir Media
Illustration - Jamie Luketa
Language - Amharic
Level - First paragraphs