ሰነፏ ማርታና ጎበዟ ራሄል
Emanda Alemayehu
ChatGPT AI

በአንድ መንደር ማርታ እና ራሄል የሚባሉ ሁለት በጣም የሚዋደዱ ጓደኛሞች ነበሩ።ሁለቱም በአንድ ትምህርት ቤትና በአንድ ክፍል ይማሩ ነበር ።ራሄል በትጋቷና በጥናቷ የታወቀች ጎበዝ ተማሪ ስትሆን ማርታ ግን ለትምህርት ትኩረት የማትሰጥ ነበረች። በዚህም ምክንያት የራሄል ቤተሰቦች በልጃቸው ሲኮሩ የማርታ ቤተሰቦች ሁሌ በልጃቸው ስንፍና ያዝኑ ነበር ።

1

ራሄል ክፍል ዉስጥ ተሳታፊ ነበረች፤ ራሄል በክፍል ውስጥ እጇን አውጥታ ስትመልስ፣ ማርታ ግን በዴስክዋ ላይ ተቀምጣ ትጫወት ነበር። መምህራኖቹም ይወዷታል። ማርታ ግን ማንም ስለማትሳተፍ መምህር አይወዳትም ነበር። አንድ ቀን መምህራቸው አሳይመንት ሰጧቸው።ከዛም መምህሩ
“ልጆች፣ የተሰጣችሁን አሳይመንት በጥንቃቄ ሠርታችሁ ለነገ አምጡ!” አሉ።

2

ራሄል ወደ ቤት እንደደረሰች የተሰጣትን አሳይመንት በትጋት ሠራች።ማርታ ግን በጨዋታ ተጠምዳ የተሰጣቸውን አሳይመንት ረሳች። በማግስቱ ማርታ ሥራዋን እንዳልሠራች አስታወሰች።

3

ራሄልም“ማርታ፣ ሥራውን ራስሽ መሥራት አለብሽ። እኔ ሁልጊዜ ልሠራልሽ አልችልም።” አለቻት።ማርታ ሥራዋን ሳትሠራ ወደ ትምህርት ቤት ሄደች። መምህሩም ሥራዋን ሲጠይቋትእንዳልሰራች ስትናገር ህልም ተማሪዎች ሳቁባት ማርታም በጣም አፈረች። አይኗም በእንባ ተሞላ።

4

ወደ ቤት ስትመለስ ማርታ እንዲህ ስዕል ምልልስ አሰበች፤“እንዲህ መቀጠል የለብኝም፤ ራሴን መለወጥ አለብኝ!” አለች።

5

ከዚያን ቀን ጀምሮ ማርታ በየቀኑ ትምህርቷን በትጋት ማጥናት ጀመረች። የቤት ሥራዋንም በጊዜው ትሠራ ነበር።

6

ቀስ በቀስ የማርታ ውጤት መሻሻል ጀመረ። መምህራኖቿ በትጋቷ ተደሰቱ። ቤተሰቦቿም በልጃቸው ለውጥ በጣም ኮሩ።

7

ማርታ ወደ ራሄል ሄዳ“ራሄል፣ በዚያ ቀን ሥራዬን ራሴ እንድሠራ ስለመከርሽኝ አመሰግናለሁ!” አለቻት።
ራሄልም ፈገግ ብላ“እኔም በአንቺ እኮራለሁ፣ ጓደኛዬ!” አለቻት

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ሰነፏ ማርታና ጎበዟ ራሄል
Author - Emanda Alemayehu
Illustration - ChatGPT AI
Language - Amharic
Level - First paragraphs