

በአንድ ትንሽ ከተማ ውስጥ በጣም አስቸጋሪ የሆኑ 3 ሽፍታዎችይኖሩ ነበር
እነዚህ ሽፍታዎች ሰዎችን ማስቸገርና ማስቃየት በጣም ያዝናናቸውና ያስደስታቸው ነበር ። አንድ ደሀ ሰው ደግሞ እነሱ በሚኖሩበት ስፍራ ላይ በግ እያገደ እና ጭራሮ እየለቀመ ቤተሰቦቹን ያስተዳድር ነበር ::
ከጊዜ ብዛት የሰውየው በጎች ቀስ በቀስ ቁጥራቸው እየቀነሰ መጣ።ምን እንደሆነ ሲያጣራ እነዛ ሽፍቶች በጎቹን እየወሰዱበት ነበር። ሰውየውምበጣም ተናደደ ተደብቆ ተከትሎአቸው በመሄድ የሱን በግ ጠብሰው ሲበሉ አየ አሁንም በጣም
ተናደደ ወደ ቤቱ በመሄድ ለሚስቱ ነገራት እሷም እባክህ ይገሉሀል እንዳትሄድ አለችው። እሱም እሷን እሺ ብሎ ወደነሱ ሄደ።
እነሱም ከቤታቸው ሲወጡ ተደብቆ እያያቸው ነበር :: ቤታቸውም በጣም የሚያስፈራ
የተቦረቦረ ዋሻ ነበረ በአስማት ይከፈት ነበር :: ሲሳም ተከፈት ሲባል ይከፈታል
ሲሳም ተዘጋ ሲሉት ይዘጋል ሽፍታዎቹ ከሄዱ በኋላ እነሱ እንዳሉት ብሎ ለመክፈት ወደ ዋሻው ተጠጋ።
ሲሳም ተከፈት ሲል ተከፈተለትና እየፈራ ወደ ውስጥ ገባ ብዙ ነገሮችንም እየበጣምም ደስ አለው እና ወርቁን ልውሰድ ወይስ ደግሞ ብሩ እያለ ትንሽ ካሰበ በኋላ ወርቁ ይሻለኛል በማለት ወርቁን ይዞ ወደቤቱ ተፈተለከ።እቤትም እንደ ደረሰ ሁሉንም ነገር ለሚስቱ ነገራት ሚስቱም አትሂድ እያለችው መሄዱ ቢያስከፋትም ሀብታም በመሆናቸውደስ አላት ከዚያም ቀን ጀምሮ ሀብታም ሆነው መኖር ጀመሩ።
የነሱን ሀብት ያየ አንድ ጎረቤቱ ግራ በመጋባት እንዴት ሀብታም ሆናችሁ ብሎ ጠየቀው ሀብታሙ ሰውየም ሁሉንም ነገር ነገረው ጎረቤቱም የተነገረው ቦታ በመሄድ ያንን አስማተኛ ዋሻ አገኘው።
እንደተባለውም "ሲሳም" ተከፈት ብሎ ገባ ባየው ነገር ስለተደሰተ ምን ብሎ በሩን ከፍቶ መውጣት እንዳለበት ጠፋበት ሽፍታዎቹም ደረሱበት ለካ ባለፈው የሰረቅከን አንተነህ ብለው አሰሩት እና በራሱ አህያ ላይ ጭነው አሰቃዩት ይባላል።

