ትንሿ ቡጡ
Etubdink Fikru
chatGPT AI

ቡጡ የሁለት ዓመት ትንሽ ልጅ ነበረች። ቤተሰቦቿ በጣም ይወዷት ስለነበር የፈለገችውን ሁሉ ይሰጧት ነበር። ቡጡም በየቀኑ ብዙ ብስኩት፣ ከረሜላ፣ ቸኮሌት፣ ኬክና አይስክሬም ትበላ ነበር። በዚህም ምክንያት ጤናማ ምግቦችን ለመብላት ፍላጎቷ ቀነሰ።

1

ቡጡ ጣፋጭ ነገሮችን በበዛ ቁጥር ጥርሷ መጎዳት ጀመረ፣ አፏም መጥፎ ጠረን ማምጣት ጀመረ። ከጊዜ በኋላም ደከመች። አንድ ቀን ከአልጋዋ መነሳት እንኳን አልቻለችም። ወላጆቿም በጣም ደንግጠው ወዲያውኑ ወደ ሐኪም ቤት ወሰዷት።

2

ሐኪሙ ቡጡን ከመረመረ በኋላ አስፈላጊውን ሕክምና ሰጣት። ከዚያም ለወላጆቿ፣ “ብዙ ጣፋጭ ነገሮች መብላቷ ጥርሷን ጎድቷል፤ እንዲሁም ጤናማ ምግቦችን እንዳትበላ አድርጓታል” አላቸው።

3

"ሐኪሙም አክሎ፣ “ስለዚህ ጣፋጭ ነገሮችን መቀነስና ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ወተትና ሌሎች ገንቢ ምግቦችን መመገብ ይገባታል” ብሎ መከራቸው። የቡጡ ወላጆችም ልጃቸውን በጣፋጭ ነገሮች በማብዛታቸው ተጸጸቱ።

4

ወላጆቿም ሐኪሙን አመሰገኑና ከዚያን በኋላ ቡጡን ጤናማ ምግቦችን እንደሚመግቧት ቃል ገቡ። ፍራፍሬና አትክልት፣ ወተትና ሌሎች ገንቢ ምግቦችን ማዘጋጀት ጀመሩ።

5

ቡጡም በጊዜ ሂደት ጤናማና ደስተኛ ልጅ ሆነች።

6

This story teaches us how nutritious vegetables and fruits are for our bodies and why we should include them in our daily diet to stay healthy and strong.

7
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ትንሿ ቡጡ
Author - Etubdink Fikru
Illustration - chatGPT AI
Language - Amharic
Level - First paragraphs