ተጓዦቹ
Etubdink Fikru
chatGPT AI

ቻሌ የ7 ዓመት ልጅ ነበር። አንድ ቀን ከአባቱ ጋር ወደ ገበያ ለመሄድ ተነሱ። አህያቸውንም ይዘው በእግራቸው መንገድ ጀመሩ። ሁለቱም በአህያዋ ላይ አልተቀመጡም ነበር።

1

በመንገድ ላይ የሚያልፉ ሰዎች አይተዋቸው፣ “አህያ እያላቸው ሁለቱም በእግራቸው ይሄዳሉ! ምን ዓይነት ቂሎች ናቸው?” ብለው ተናገሩ። ቻሌና አባቱም ይህን ሰምተው ሁለቱም በአህያዋ ላይ ተቀመጡ።

2

ትንሽ እንደተጓዙ ሌሎች ሰዎች አገኟቸውና፣ “ይህ ጭካኔ ነው! ሁለታችሁም በአንዲት አህያ ላይ ተቀምጣችሁ ትጎዷታላችሁ!” አሉ። ቻሌና አባቱም ይህን ሰምተው አባቱ ከአህያዋ ወርዶ ቻሌን ብቻውን እንዲቀመጥ አደረገ።

3

ጥቂት እንደተጓዙ ሌሎች ሰዎች አገኟቸው። “አባቱ በእግሩ እየሄደ ልጁ በአህያ ላይ መቀመጡ እንዴት ይሆናል?” ብለው ተቹአቸው። ቻሌና አባቱም ይህን ሰምተው ቻሌ ከአህያዋ ወርዶ አባቱን አስቀመጠው።

4

ከዚያም ሁለቱም ተመካከሩና፣ “ሰዎች የምናደርገውን ሁሉ ይተቻሉ። ሁሉንም ሰው ለማስደሰት መሞከር አይቻልም” ብለው ወሰኑ። ስለዚህ ከአህያዋ ወርደው ሁለቱም በእግራቸው መሄዳቸውን ቀጠሉ።

5

ሁሉንም ሰው ለማስደሰት መሞከር አይቻልም” ብለው ወሰኑ። ስለዚህ ከአህያዋ ወርደው ሁለቱም በእግራቸው መሄዳቸውን ቀጠሉ።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ተጓዦቹ
Author - Etubdink Fikru
Illustration - chatGPT AI
Language - Amharic
Level - First paragraphs