ባለወርቃማ እንቁላል ጣይ ዶሮ
Yeabfire Dagmawi
chatGPT AI

ከብዙ ዓመታት በፊት በአንድ ቆንጆ መንደር አንድ ደሃ አርሶ አደር ከሚስቱ እና ከልጆቹ ጋር ይኖር ነበር። በየቀኑ ጠዋት ተነስተው ለልጆቻቸውና ለቤተሰባቸው ለመብላት እና ለመኖር በትጋት ይሠሩ ነበር።

1

አንድ ቀን አርሶ አደሩ ወደ ዶሮዎቹ ሄዶ እንቁላል ለመሰብሰብ ሲጀምር፣ አንድ ያልተለመደ ነገር አየ።

እንቁላሉ እንደ ተራ እንቁላል ሳይሆን ወርቅ ነበር!

“ይሄ ምንድነው?” ብሎ በመደነቅ ወርቃማውን እንቁላል ይዞ ወደ ቤት ሮጠ።

“ሚስቴ! ሚስቴ! እዚህ ነይ! ይህን ተመልከቺ!” አላት።

2

ሚስቱም በመገረም እንቁላሉን ተመለከተች።
“ይሄ ወርቅ ነው!” አለች።
ሁለቱም በጣም ተደሰቱ። ወርቃማውን እንቁላል ሸጠው ለቤተሰባቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ለመግዛት አቀዱ።
በማግስቱም ዶሮዋ እንደገና አንድ ወርቃማ እንቁላል ጣለች።

3

በማግስቱም ዶሮዋ እንደገና አንድ ወርቃማ እንቁላል ጣለች።

እንዲሁም በየቀኑ ዶሮዋ አንድ ወርቃማ እንቁላል መጣል ጀመረች።

ቤተሰቡም ቀስ በቀስ ከድህነት ወጥቶ በሰላምና በደስታ መኖር ጀመረ።

4

አርሶ አደሩ እና ሚስቱ በቀን አንድ እንቁላል ብቻ ማግኘታቸው ከጊዜ በኋላ ትንሽ አሰለቻቸው።

አንድ ቀን ሚስቱ፦

“ይህች ዶሮ በሆዷ ውስጥ ብዙ ወርቅ ይዛ ብትሆንስ? ለምን አንድ ቀን አርደን ዉስጧን አይተን ሁሉንም ወርቅ አንድ ጊዜ አንወስድም?” አለች።

5

አርሶ አደሩም በስግብግብነት ተስማማ።

“እውነት ነው! በአንድ ጊዜ ብዙ ወርቅ ብናገኝ በጣም ሀብታሞች እንሆናለን!” አለ።

እነሱም ዶሮዋን ይዘው ውስጧ ብዙ ወርቅ እንዳለ ለማየት ሞከሩ።

6

ነገር ግን...

ውስጧ እንደ ሌሎች ዶሮዎች ብቻ ነበር። ምንም ወርቅ አልነበረም!

ያን ጊዜ ሁለቱም በጣም አዘኑ።

አሁን ዶሮዋም የለችም፤ የወርቅ እንቁላሉም የለም።

7

አርሶ አደሩ ራሱን ይዞ፦

“እኛ በስግብግብነታችን በየቀኑ የምናገኘውን ወርቅ አጣነው!” ብሎ በጣም ተጸጸተ።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ባለወርቃማ እንቁላል ጣይ ዶሮ
Author - Yeabfire Dagmawi
Illustration - chatGPT AI
Language - Amharic
Level - Longer paragraphs