ድንችና ካሮት
Bezawit Wogayehu
Chat GPT AI

ከዕለታት አንድ ቀን ድንች አንዲት ዶሮ ገዛ። ዶሮዋም በየቀኑ የሚያብረቀርቁ የአልማዝ እንቁላሎችን መጣል ጀመረች። ድንችም እንቁላሎቹን በመሸጥ በጣም ሀብታም ሆነ።

1

ይህን የሰማው ካሮት በጣም ቀና። “ያቺን ዶሮ ብወስዳት እኔም ሀብታም እሆናለሁ” ብሎ አሰበ። ስለዚህ ዶሮዋን ለመስረቅ እቅድ አወጣ።

2

አንድ ሌሊት ድንች ተኝቶ እያለ ካሮት በጥንቃቄ ወደ ቤቱ ገባ። ዶሮዋንም ይዞ ሊወጣ ሲል ዶሮዋ በኃይል “ቆኮሪኮ! ቆኮሪኮ!” ብላ ጮኸች። ድንችም ከእንቅልፉ ነቅቶ ዱላ ይዞ በፍጥነት ሮጠ።

3

ካሮት ግን ዶሮዋን ይዞ ሊያመልጥ ሞከረ። ድንችም ዶሮዋን ማጣቱን ሲያይ በጣም አዘነና አለቀሰ። ከዚያም ለሰዎች ነግሮ እርዳታ ጠየቀ። ሰዎቹም ካሮትን በመፈለግ አገኙት።

4

ካሮት የድንችን ዶሮ ሊሰርቅ እንደነበር ታወቀ። በስህተቱም ምክንያት ተቀጣ። ከብዙ ዓመታት በኋላ ከተቀጣ በኋላ ወደ ድንች ተመልሶ፣ “ይቅር በለኝ። ስለቀናሁና ስለሰረቅኩ በጣም ተጸጽቻለሁ” ብሎ ይቅርታ ጠየቀው።

5

ድንችም የካሮትን ንስሐ ተመልክቶ ይቅር አለው።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ድንችና ካሮት
Author - Bezawit Wogayehu
Illustration - Chat GPT AI
Language - Amharic
Level - First paragraphs