ጎበዟ ልዕልት
Nuhamin Chalewu
ኑሀሚን ቻለው

በአንድ ትልቅ ቤተ መንግስት ውስጥ የንጉስ እና የንግስት ልጅ ነበረች። ስሟ ሜሎና ትባላለች። በጣም ጎበዝ ነበረች። ከእንቅልፋ ስትነሳ አልጋዋን ታነጥፋለች። ልብሷንም ትለብሳለች። ቤተሰቦቿም ይወዷታል

1

አንድ ቀን አቧቷ በጠና ይታመማል። ብዙ ሀኪሞች ቢያዩትም መፍትሔ ሊሰጡት አልቻሉም ። አንድ አሮጊት መጣችና ስታየው መድሀኒቱ የሚገኘው አንድ ተራራ ላይ የሚገኘው የዛፍ ፍሬ ነው። እሱም ከመጣለት ይድናል ተባለ። ነገር ግን እዛ የሚገኘው አስፈሪ ተናዳፊ እባብ አለ። ብዙ ሰው ሄዶ ሞቷል ተጠንቀቁ አለቻቸው። እነሱም በጣም ፈሩ። ጠባቂዎቹም ሸሹ። ጎበዟ ልዕልት አባቴማ አይሞትም

2

እሄዳለሁ አለች። እናቷም ተይ ትሞቻለሽ ብትላትም እሄዳለሁ አለች።ስትሄድ በመንገዷ ላይ አንድ ሽማግሌ አገኘች። ሽማግሌውም "እባክሽ ልጄ ይህንን ማሰሮ ቤት ትወስጂልኛለሽ" አላት። እሷም "እሺ እወስደዋለሁ" አለቻቸው። እየሄዱ እያሉ ወዴት እየሄድሽ ነበር አሏት። እኔ የምሄደው አባቴ ታሞ አንዲት አሮጊት አንድ ተራራ ላይ የሚገኘውን የዛፍ ፍሬ ካመጣሽለት አባትሽ ይድናል ተብዬ ወደ

3

ተራራው እየሄድኩ ነዉ አለቻቸው አዎ ግን ተጠንቀቂ አስፈሪ ተናዳፊ እባብ አለ። እንዴት በብልሀት ማለፍ እንዳለብሽ እቤት ቁጭ ብለን እነግርሻለሁ ሲሏት እሷም እሺ አባባ እንሂድ ብለዉ ጉዟቸውን ቀጠሉ። እንደደረሱም ነይ ቁጭ በይ ብለዋት እሺ ብላ ተቀመጠች። እይው ልጄ በጣም ጎበዝ እና ታታሪ ልጅ ነሽ። ይህንን አስፈሪ እባብ እንዴት መጋፈጥ እንደምችዪ መስማት ትፈልጊያለሽ? ሲሏት

4

አዎ አባባ አለች። ልጄ እዛ ድብቅ ዋሽንት አለ እሱን ከነፋሽለት እባቡ ይተኛል ያንን ፍሬ መውሰድ ትችያለሽ ሲሏት እሷም ደስ አላት። እሷም ፈጥና ሄደች። እዞም እንደደረሰች አበባ ያሏትን አስታውሳ ዋሽንቱን ፍለጋ መሄድ ጀመረች። ዋሽንትም መንፋት አትችልም ነበር ነገር ግን አባቴ መሞት የለበትም ብላ ባትችልም መንፍት ጀመረች ቀስቀስ እያለ እጣቡም ተኛ። ከዛም የዛፍ ፍሬውን ወስደች

5

እናም እቤት እንደደረሰች ለአሮጊቷ ሰጠቻት። አይጊቷም ቀምማ መድሀኒቱን ለአባቷ ስጠችው። እሱም ዳነ። እና ጎበዟ ልዕልት ጎበኋ ልዕልት እያሉ አሞገሷት። እሷም ደስ አላት።

6

መልእክት:
ልጆችዬ ጎበዝ ታታሪ መሆን አለብን።
ቤተሰብም ማክበር አለብን።
በጎ የስራ በጎ ይደረግለታል።

7
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጎበዟ ልዕልት
Author - Nuhamin Chalewu
Illustration - ኑሀሚን ቻለው, Kenneth Boyowa Okitikpi
Language - Amharic
Level - First paragraphs