ንጹሕ አካባቢ
Firehiwot Masresha
Chat GPT AI

ደስ በሚሉ አረንጓዴ ተራሮች በተከበበች ውብ መንደር ውስጥ “ቱቱ” የሚባል በጣም ጎበዝና ተጫዋች ጥንቸል ነበረ። ቱቱ ዘወትር ከጓደኞቹ ከዝንጀሮው "ቦቦ"ና ከወፎቹ ጋር በመንደሯ መሃል ባለው ትልቅ የዛፍ ጥላ ስር መጫወት በጣም ይወድ እና ያስደስተዉም ነበር።

1

አንድ ቀን ግን በጨዋታቸው መካከል ቦቦ በልቶ የጨረሰውን የሙዝ ልጣጭ፣ ቱቱ ደግሞ የጠጣበትን የፕላስቲክ ሀይላንድ እዚያው የተቀመጡበት ሳር ላይ ጥለውት ሄዱ። ሌሎች እንስሳትም እንደዚሁ ያገኙትን ቆሻሻዎች በየቦታው መጣል ጀመሩ።

2

ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ያች አረንጓዴና ውብ መንደር በቆሻሻ ተሞላች! በየቦታው ያለው የቆሻሻ ክምችት ደስ የማይል ጠረን ማምጣት ጀመረ። የቆሻሻውም ሽታ ደስ ስለማይል ወፎቹ መዘመር አቆሙ፤ ዝንቦችና ቢንቢዎች በየቦታው በረከቱ። በሽታም ተስፋፋ ሁሉም እንሰሳት ታመሙ።

3

በሚቀጥለው ቀን ቱቱና ቦቦ ለመጫወት ሲወጡ፣ ሁለቱም ሆዳቸውን አሟቸው፤ የመጫወቻቸውም ቦታ በሚያስጠላ ሽታ ምክንያት ደስ የማይል ሆነ። ቱቱ አዝኖ የተቀመጠበትን ቦታ ሲመለከት፣ በየቦታው የተቀመጡት ቆሻሻዎች አካባቢያቸውን እንዳበላሹት ና በሽታ ያመጡባቸው እነዚህ መሆናቸዉን ተረዳ።

4

ወዲያውኑ ቱቱ ቦቦንና ሌሎችንም የአካባቢዉን እንስሳት ሰበሰባቸውና፤ “ጓደኞቼ! አካባቢያችንን ያቆሸሸነው እኛው ነን፤ አሁን ደግሞ ታምመናል። አካባቢያችን ንጹሕ ካልሆነ እኛም ጤነኞች ልንሆን አንችልም! ስለዚህ ሁላችንም አብረን መንደራችንን እናጽዳ” አላቸው።

5

ሁሉም እንስሳት በቱቱ ሀሳብ ተስማሙ። ወዲያዉም ቦቦ የዛፍ ቅርንጫፎች ይዞ መጥረጊያ አዘጋጀ፤ ቱቱና ሌሎች እንስሳት ደግሞ በየቦታው የወደቁትን የፕላስቲክ ሀይላንዶችና ወረቀቶች ለቅመው በትልልቅ ቅርጫቶች ውስጥ ከተቱ። ወፎቹም በከንፈሮቻቸው ትናንሽ ቆሻሻዎችን እየለቀሙ ረዱ።

6

በአንድነት ሰርተውም አካባቢውን ሲያጸዱ፣ መንደሯ እንደገና ደምቃና አበቦቿ አብበው መታየት ጀመሩ! ደስ የሚለውም መዓዛ ተመለሰ ፤ የበሽታውም መንስኤ ጠፋ።

7

ታዲያ በዚያ ቀን ቱቱና ጓደኞቹ አንድ ትልቅ ህግ አወጡ፦
“ቆሻሻን ሁልጊዜ በቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ውስጥ ብቻ እንጥላለን!”አሉ።
ከዚያች ቀን በኋላም መንደራቸው እንደገና በደስታና በጤና ተሞላች።

8

ከዚህ ተረት የምንማረዉ ተባብሮ መስራትን፣ ጤናማ ለመሆን የአካባቢን ንፅህና የራሳችንን ንፅህና መጠበቅ እንዳለብን ነዉ።

9
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ንጹሕ አካባቢ
Author - Firehiwot Masresha
Illustration - Chat GPT AI
Language - Amharic
Level - First paragraphs