አስማተኛዉ የጣት ቀለበት
Firehiwot Masresha
Chat GPT AI

አበቦች በበቀሉበትና ወፎች በሚዘምሩበት በአንድ ውብ ማራኪ መንደር ውስጥ “ልዑል” የሚባል ደግና ታታሪ ልጅ ነበረ። ልዑል ሁልጊዜ ሰዎችን መርዳት፣ ከጓደኞቹ ጋር በደስታ መጫወትና አረጋውያንን ማከበር እና መታዘዝ ይወድ ነበር።

1

አንድ ቀን ልዑል ከትምህርት ቤት ወደ ቤት ሲመለስ፣ ከትልቅ የዋርካ ዛፍ ስር አንድ የሚያብረቀርቅ ነገር ተመለከተ። ቀረብ ብሎ ሲያይ ወርቃማ የሆነና አረንጓዴ ዕንቁ ያለዉ ውብ የጣት ቀለበት ነበር! ልዑል ቀለበቱን ከአቧራው ላይ አንስቶ እጁ ላይ ሲያደርገዉ፣ በድንገት ቀለበቱ በደማቅ ብርሃን ፈነጠቀና በጥሩ ድምፅ መናገር ጀመረ!

2

“ሰላም ልዑል! እኔ አስማተኛ የጣት ቀለበት ነኝ” አለው። “የአንተን ደግነትና ታታሪነት ስላየሁ ፍላጎቶችህን ልፈጽምልህ ዝግጁ ነኝ። ምን ትመኛለህ?” አለው።

3

ልዑልም ጥቂት ካሰበ በኋላ ፈገግ ብሎ “መጀመሪያ... በመንደራችን ያሉ ህፃናት በሙሉ የሚጫወቱበት የጭቃ አሻንጉሊት ሳይሆን ብዙ አዲስ ኳሶችና የመጫወቻ እቃዎች እንዲኖረን እፈልጋለሁ” አለ። ቀለበቱም ወዲያውኑ አበራ፤ በቅጽበትም በመንደሩ ሜዳ ላይ በቀለማት ያሸበረቁ ኳሶችና መጫወቻዎች ተሞሉ።

4

በሁለተኛነት ደግሞ “በመንደራችን ያሉ አያቶችና አባቶች የሚጠጡት ንጹሕ ውኃ ቅርብ ቦታ እንዲሆንልን እፈልጋለሁ” አለ። ቀለበቱም እንደገና ሲያበራ፣ በመንደሩ መሃል ንጹሕ ውኃ የሚያመነጭ ጥልቅ ምንጭ ተከፈተ።

5

አስማተኛዉ ቀለበት በጣም በመደነቅ “ልዑል! ሁለቱንም ምኞቶችህን ለሌሎች ሰዎች ጥቅም አዉለሃል፤ የመጨረሻውን ምኞትህን ደግሞ ለእኔ ልታደርግልኝ ትችላለህ?” አለው። ልዑልም “ምን አደርግልህ ይሆን?” ብሎ ጠየቀዉ።

6

ቀለበቱም “እኔ ለብዙ ዘመናት በዚህ ዛፍ ስር ተቀብሬ ነበር፤ አሁን ግን ነፃ ወጥቼ ወደ ተፈጥሮዬ መመለስ እፈልጋለሁ። ከመስኩ አፈር ውስጥ ብትመልሰኝና ነፃ ብታወጣኝ ደስ ይለኛል” አለው። ልዑልም አላንገራገረም፤ ቀለበቷን በጥንቃቄ አውልቆ ከቀይ አፈሩና ከአበቦቹ መካከል መልሶ ቀበራት።

7

ቀለበቱም ከመሰናበቱ በፊት “ልዑል! እውነተኛው አስማት እኔ ዘንድ ሳይሆን ያንተ ደግነትና መልካም ልብ ውስጥ ነው ያለው! ደግነትህ ሁልጊዜ ብሩህ ያደርግሃል” አለውና ጠፋ።
ከዚያን ቀን ጀምሮ ልዑልና የመንደሩ ህፃናት በደስታ እየተጫወቱ፣ አረጋውያኑም ንጹሕ ውኃ እየጠጡ በደስታና በፍቅር አብረው ኖሩ።

8

This story teaches us, to keep our promises,appreciate those who help us, respect their wishes. Just as Luel respected the magical ring's wish and set it free, we should also respect, appreciate, and help those who have helped us.

9
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
አስማተኛዉ የጣት ቀለበት
Author - Firehiwot Masresha
Illustration - Chat GPT AI, ፍሬህይወት ማስረሻ
Language - Amharic
Level - First paragraphs