ናሆም እና ምኞቶቹ
Firehiwot Masresha
Chat GPT AI

በአንድ ውብ መንደር ውስጥ “ናሆም” የሚባል በጣም ጎበዝና ንቁ ልጅ ነበር። ናሆም ዘወትር አመሻሽ ላይ ከአያቱ ጋር በደጅ ተቀምጦ ከዋክብትን እያየ ማወራትና ማለም በጣም ይወዳል::

1

አንድ ቀን አያቱ ፈገግ ብለው “ናሆም ልጄ... አድገህ ትልቅ ስትሆን ምን መሆን ትፈልጋለህ?” ብለው ጠየቁት።ናሆምም ጥቂት አሰበና “አያቴ! እኔ ብዙ ነገሮች መሆን እፈልጋለሁ። ለምሳሌ ዶክተር ሆኜ የታመሙ ሰዎችንና ህፃናትን ማከም እፈልጋለሁ! ሰዎች ከሕመም ሲገላገሉ ማየት ደስ ይለኛል” አለ።

2

አያቱም “በጣም ጥሩ ሕልም ነው ልጄ! ዶክተር መሆን ሰዎችን የሚረዳ ትልቅ ሙያ ነው” አሉት።ናሆምም ቀጠል አድርጎ “ነገር ግን አያቴ ... አስተማሪም መሆን እፈልጋለሁ! ለልጆች አዳዲስ ነገሮችን፣ ደግነትንና እውቀትን ማስተማር ደስ ይለኛል።

3

ደግሞስ መሃንዲስ ብሆን? ትልልቅ ሕንፃዎችን፣ መንገዶችንና ድልድዮችን ሰርቼ ሀገሬን ብገነባስ?” እያለ በጉጉት ዓይኖቹ አበሩ።

4

አያቱም የናሆምን እጅ ይዘው፣ “ልጄ ናሆም! እነዚህ ሁሉ በጣም ድንቅና አስፈላጊ ሙያዎች ናቸው። ነገር ግን ከሁሉም በላይ ልትሆን የሚገባህ ዋናው ነገር ምን እንደሆነ ታውቃለህ?” ብለው ጠየቁት።
ናሆም አፉን ከፍቶ “ምን ይሆን አያቴ?” አለ።

5

አያቱም ፈገግ ብለው “የትኛውም ሙያ ውስጥ ብትሰማራ፣ መጀመሪያ ‘ደግ፣ ታማኝና ትጉህ ሰው’ መሆን አለብህ! ጥሩ ሰው ከሆንክ፣ የምትሰራው ማናቸውም ሥራ ለሰዎች ብርሃንና ደስታ ይሆናል። ዋናው ነገር አሁኑኑ በትምህርትህ መበርታት፣ አባቶችን ማከበርና ሌሎችን መረዳት ነው” አሉት።

6

ናሆም የአያቱን ምክር በደስታ ተቀበለ። ከዚያች ቀን ጀምሮ “ትልቅ ስሆን ደግና ጎበዝ ሰው እሆናለሁ ሳድግ ደግሞ ሀገሬንና ህዝቤን እረዳለሁ!” ብሎ ለራሱ እቅድ አወጣ።

7

ከዚህ ተረት የምንማረዉ:-
ትልቅ ቦታ ከመድረስ በላይ ደግ፣ ታማኝና እውነተኛ ሰው መሆን እንደሚስፈልግ
በትምህርት መበርታት፤ ለሕልማቸው ስኬት አሁኑኑ በትምህርታቸው መጣር እንዳለብን ይህ ተረት ያስተምረናል።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ናሆም እና ምኞቶቹ
Author - Firehiwot Masresha
Illustration - Chat GPT AI, ፍሬህይወት ማስረሻ
Language - Amharic
Level - First paragraphs