የመልካም አባት ኑዛዜ
Gifti Kbeb
ጊፍቲ ክበብ

ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ገበሬ በጠና ታመመና ሞቱ ሲቃረብ ልጆቹን አስጠራቸውና አንድ ትልቅ እና ልጆቹ እንዲጓጉ የሚያደርግ ኑዛዜ ተናዘዘላቸው።

1

ልጆቹንም ካስጠራቸው በኋላ በአጠገቡ አቁሞ ልጆቼ ሆይ አሁን የምነግራችሁን ኑዛዜ ልብ ብላችሁ አዳምጡ ብሎ ኑዛዜውን ቀጠለ አሁን በሽታው ስለጠናብኝ ከቦታችን የደበቁትን ወርቅ ቦታውን ላመለክታችሁ አልተቻለኝምና ቦታውን በመደዳው ቆፍራችሁ እንድትፈልጉ አላቸው።

2

ልጆቹም የሞተውን አባታቸውን ከቀበሩ ብሀላ ያባታቸውን ኑዛዜ ተከትለው ዶማቸውንና አካፋቸውን ይዘው ወርቁን ለማግኘት ቦታቸውን ዳር እስከ ዳር ቆፈሩት ነገር ግን አባታቸው እንደዚህ ያላቸው ልጆቹ ስራ እንዳይፈቱ ብሎ ነው እንጂ በርግጥ ወርቅ ደብቆ አይደለም።

3

ልጆቹም ወርቁን ባጡ ጊዜ እንዲህ ወርቁን ካጣነው የቆፈርነውን ቦታችንን ስንዴ እና ገብስ እንዝራበት ብለው ዘሩበትና የዘሩት ጥሩ ሆነላቸው። የዘሩትን ፍሬም ጥሩ ሆኖ አፈራላቸው። ፍሬያቸውንም እየሸጡ ወርቃቸውን ይሰበስቡ ጀመር። ያን ጌዜ ጥቅማቸውን ካወቁ በኋላ ልጆቹ ስራ እንዳይፈቱ መሬቱ እንዳይቦዝን ብሎ ነው እንጂ አባታቸው ወርቅ እንዳልደበቀ ተረዱ ይባላል

4
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የመልካም አባት ኑዛዜ
Author - Gifti Kbeb
Illustration - ጊፍቲ ክበብ
Language - Amharic
Level - First paragraphs