

በድሮ ጊዜ በአንድ መንደር ውስጥ ፈረስ እና ፍየል ይኖሩ ነበር ። ከዛም አንድ ቀን ሁለቱም ከአካባቢያቸው ርቀው ለመጓዝ ወሰኑ። በጉዟቸውም ፈረስ በፍየል ላይ አንቺ በጣም አጭር ቁመተ ቢስ እያለ ያላግጥባት ነበር። እሷም መልክ እና ቁመት ሳይሆን ዋናው ብልሀት ነው ትለው ነበር። ፈረሱም ይስቅባት ነበር።
ብዙ ከተጓዙ ቡሀላ ሁለቱም የረሀብ ስሜት ተሰማቸው እና ምግብ ፍለጋ ጀመሩ። ፈረስም አንድ ረዘም ያለ ዛፍ አገኘ ። ከዛም መብላት ጀመረ ። ፍየልም ትንሽ ቅጠል ስጠኝ ስትለው እሱም ስጠግብ እሠጥሻለሁ አላት። እሷም እሺ ብላ መጠበቅ ጀመረች ። ፈረሱም ሲጠግብ መሬት ላይ ጋደም አለ።
ፍየሏም ፈረስ ስጠግብ እሠጥሻለሁ አላልከኝም እንዴ? ስትለዉ ፈረሱ አንቺ እኮ ይሄኔ ረጅም ብትሆኚ ኖሮ መብላት ትችዪ ነበር። ጠዋትም ስነግርሽ ዋናው ብልሀት ነዉ እያልሽ እጥረትሽን ሰትሸፋፍኚ ነበር አላት። እሷም ትንሽ ቅጠል ስጠኝ ብላ እያለቀሰች መለመን ጀመረች። እሱም እየሳቀባት ተኛ ፍየልም ረሀቧን ተቋቁማ ተኛች። በቀጣዪ ቀን ጉዟቸውን ጀመሩ በመንገዳቸውም ላይ አንድ
በአጥር የታጠረ ተክል አገኙ። ከአጥሩ ታችም ትንሽ ክፍተት ነበር። ፍየልም ያንን ክፍተት ስታይ ሮጣ ገባች። ስትገባም ብዙ የተክል አይነቶች አገኘች እየቀጠፈችም መብላት ጀመረች።ፈረስ ግን በቀዳዳው መግባት ስላልቻለ ፍየል ትንሽ ቅጠል ስጭኝ እያለ ለመናት።
እሷም ትናንት ያደረጋትን በማስታወስ ምንም አይነት ቅጠል እንደማትሰጠው ተናገረች። እሱም እባክሽ ፍየል ስጪኝ እያለ ለመናት ከዛም እሷ ስጠግብ እሰጥሀለሁ አለችው። ከጠገበች ብሀላም አረፍ ስትል ፈረሱም ፍየል ስጠግብ ትንሽ ቅጠል እሰጥሀለሁ አላልሽም ሲላት እሷም በጣም ደግ ስለነበረች ትንሽ ቅጠል ሰጠችው ፈረሱም አመስግኖ ከበላ ብሀላ ፍየልን እባክሽ ይቅርታ አድርጊልኝ ብሎ
ሲያለቅስ ፍየልም እሺ ብላ ይቅርታውን ተቀበለች ከዛም ሁለቱም በደስታ መኖር ጀመሩ።
Wecanlearn we should never mock, tease, or make fun of anyone for who they are or how they are naturally. Most importantly, we should have a forgiving heart. We should be willing to ask for forgiveness and also be ready to forgive others.

