ትሁቱ ዲቡ
Tesfamichael Hailu
Netsanet Wasihun

በድሮ ጊዜ አንድ ዲቡ የሚባል የስምንት አመት ልጅ በደብረብርሃን ከተማ  ይኖር ነበር።

1

ድሮ ደብረብርሃን ትንሽ ከተማ ስለነበረች አብዛኛው ሰው እርስበርሱ ይተዋወቃል፣ዲቡ ቁመቱ አጭር ይሁን እንጂ ለቤተሰቦቹና ለሰፈሩ ፈጣን እና አስተዋይ ልጅ ነበር።

2

"ሲጠሩት አቤት!፣ሲልኩት ወዴት?" የሚል ጎበዝ ልጅ።

3

ከእለታት አንድ ቀን አንድ የሰፈሩ በእድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ገበያ ልከውት ሲመለስ ያልታወቁ መንገደኞች ጠልፈው ይወስዱታል።

4

በዚህም የተደናገጡት ቤተሰቦቹና የአካባቢው ሰዎች ዲቡን ፍለጋ ይወጣሉ በፍለጋቸውም እድል ቀንቷቸው ሌቦቹ ዲቡን በአህያ ጭነው ከከተማ ይዘዉት ሊወጡ ሲሉ ይገኛሉ።

5

በህብረተሰቡ ጥቆማ ወንጀለኞቹ ተይዘው ለህግ እንዲቀርቡ ተደረገ። ዲቡም ከህብረተሰቡ እና ከቤተሰቡ ጋር በሰላም በደስታ መኖር ጀመረ።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ትሁቱ ዲቡ
Author - Tesfamichael Hailu
Illustration - Netsanet Wasihun
Language - Amharic
Level - First paragraphs