መንትዮቹ
Tesfamichael Hailu
Netsanet Wasihun

ናሆም እና ኤዶም በአንድ ቀን የተወለዱ መንታያ እህትና ወንድም ናቸው። መንትያ ማለት ከአንድ ማህጸን በእኩል ቀንና ሰአት መወለድ ማለት ነው።
ናሆም እና ኤዶም ከመልካቸው መመሳሰል ውጪ በባህሪያቸው ፍፁም የተለያዩ ናቸው።

1

ናሆም ችኩል እና ከሰፈር ጓደኞቹ ጋር ጨዋታዎችን አብዝቶ የሚወድ ሲሆን እንደ ኳስ ፣ አባሮሽ እና ብይ የመሳሰሉ ጨዋታዎችን ሲያዝወትር በትምህርቱም ደከም ያለ ነው።

2

ኤዶም ግን ከትምህርቷ ውጪ ብዙ ጊዜዋን የቤተሰቦቿን ኮምፒውተር እና ስልክ በመጠቀም ቨርችዋል ጌሞችን በመጫወት ፣ የአኒሜሽን ፊልሞችን በመመልከት የቋንቋ ክህሎቷን ከማሳደጓም በላይ ንቁ እና አስተዋይ እንዲሁም በትምህርቷ የዋንጫና ሜዳልያ ተሸላሚ ነች።

3

በዚህም ምክንያት ብዙ ጊዜ ናሆም በእህቱ በጣም ጎበዝ መሆን ስለሚቀና እና ወላጆቻቸው ሁልጊዜ ኤዶምን በጉብዝናዋ ሽልማት ይሸልሟታል።

4

ናሆምም የጨዋታ ጊዜውን ቀንሶ በርትቶ ማጥናት እንዳለበት በመረዳት ማጥናት እና ለትምህርቱ ጊዜ መስጠት ጀመረ።

5

ኤዶምም ሰፊ ጊዜዋን ኮምፒውተር እና ስልክ ላይ መቆየቷ የአይን ህመም እያመጣባት ስለሆነ በመጠኑ መጠቀም እንዳለባት ትረዳለች። መንትዮቹ ችግሮቻቸውን ፈተው በሰላም መኖር ጀመሩ።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
መንትዮቹ
Author - Tesfamichael Hailu
Illustration - Netsanet Wasihun
Language - Amharic
Level - Longer paragraphs