

በድሮ ጊዜ በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩሁለት እህትማማቾች እና አንድ አባት ነበሩ።አባትየውም ሁሌ ለእራት ሾርባ እና ዳቦይዞ ይመጣ ነበር።አባትየውም እራት እየበሉ ሳለ እንዲህ አላቸው ከአሁኑ በኋላ ስራ መስራት አልችልም ፤ምክንያቱም አቅሜ ደክሟል፡፡ስለዚህም ስራ ተከፋፍላችሁ እንድሰሩ ብሎ ነገራቸው።
ሁለቱ እህትማማቾች ተመካከሩ አንዷ በጣም ሰነፍ ስለሆነች የቤቱን ስራ መስራት አትችልም፡፡ የቤት ስራ ከመስራት ይልቅ ራሷን በመስታወት ማየት እና መንከባከብ ብቻ ነው የምትወደው፡፡ አንዷ ደግሞ የቤቱን ስራ በሙሉ የምትሠራው እናም በጣምጎበዝ፣ ታዛዥ ፣የሰው ምክር የምትሰማ ነበረች።ሰነፏ የቤቱን ስራ ልትሰራ ጎበዟ ደግሞ በጠዋት ተነስታ ስራ ልትፈልግ ተስማሙ።
ጎበዟም ልጅ በጠዋት ተነስታ ውሃና ምግብ ይዛ ልትሄድ እንደሆነ ለአባቷ ነገረችው።አባቷም " የኔ ልጅ በመንገድሽ እርዳታ የሚጠይቅሽን በሙሉ እርዳታ ስጭ በአግባቡ ስራሽን ስሪ አለቃሽ የሚልሽን ስሚ" ብሎ መክሮ ሸኛት።
እሷም ብዙ ከተጓዘች በኋላ አንድ ዛፍ አገኘች፡፡ እሱም ልጄ እባክሽ እርጅኝ አላት።እሷም ምን አድርጌ አለች እሱም ካለሽ ውሃ ላይ ትንሽ አጠጪኝ አላት፡፡ እሷም እሺ ብላ አጠጣችው፡፡ እሱም አመሰገናት እና ተለያዩ።
ትንሽ ከተጎዘች በኋላ አንድ ትልቅ ቤት አገኘች፡፡ቤቱን አንኳኳች እንዴትሴት ምን ፈልገሽ ነው ? አለቻት፡፡እርሷም ስራ እንደፈለገች ብቻ ነገረቻት፡፡ ሴትዮዋም ተስማምታ አንዱን ክፍልእንድታፀዳው እንዳትነካው ምንም ነገር እንዳታረገው ነገረቻት እሷም ተስማምታ ስራውን ጀመረች ከዛም ብዙ ዓመታት አብረው ኖሩ፡፡ አንድ ቀንም አባቷ እንደናፈቃት እናም መሄድ እንዳለባት ነገረቻት።
ሴትዮዋም እየተከፋችም ቢሆን እሺ አለቻት ከሄዷ በፊት ያንን ክፍል ማየት እንደምፈልግ ጠየቀቻት አይ ማየት አልፈልግም አለቻት፡፡ሴትየዋም እየተገረመች ክፍሉን
ከፍታ ካለው ብዙ ወርቅ ላይ ትንሽ ወርቅ ይዛ መታ እስከ ዛሬ ድረስ የለፋሽበት እናም ለታማኝነትሽ ነው ብላ ሰጠቻት፡፡ እሷም በጣምተደስታ ሄደች፡፡ ትንሽ ከተጓዘች በኋላ ያኔ የረዳችው ዛፍ የወርቅ አፕል አፍርቶ ነበር።
እሱም የወርቅ አፕል እንድትወስድ ነገራት፡፡ ምን ስላደረኩልህ አለችው፡፡ እሱም የዛኔ ስለረዳሽኝ ይህ ወርቅ ይገባሻልአላት እሷም እየተደሰተች ወደ ቤቷ ሄደች። ቤቷም ስደርስ ቤቱቆሽ ሾ ነበር።እህቷም ጓሮ ነበረች ቤቱን ማፅዳት ጀመረች አባቷምመጣየገጠማትን ሁሉ ነገረችው እሱም በጣም ተደሰተ እናም የደስታ አንባ አነባእህቷም የገጠማትን ሰማች እሷም በጠዋትተነስታ ለመሄድ ወሰነች።
በነጋታውም ተነስታልትሄድ እንደሆነ ለአባቷ ንገረችው አባቷም መከረእናሸኛትትንሽከተጓዘችበኋላ አንድዛፍ አገኘች ዛፍምእርጂኝ አላት እሷም ምን አርጌ አለችው እሱም ካለሽ ውሃ ላይ ትንሽ አካፊኝ አላት እኔ የምጠጣው ነው። ስለዚህ አልሰጥህም አለችው እናም ጥለው ሄደች ትንሽ ከተጓዘች በኋላ አንድ ቤት አገኘች ውንም አንኳኳች ምን ፈልገሽን አለቻት እሷም ስራ ፈልጌ ነው አለች ሴትየዋም
ተስማማት ግን አንዱን ክፍል ምንም ነገር ቢሆን መክፈት እንደማትችል ነገረቻት፡፡እሷም የወርቁ ክፍል ነው ብላ ስላሰበች ወዲያውኑ ከፍታ ገባች፡፡ ስትገባ ም ጉንዳኖች ነበር እናም እየነካከሱ አስወጧት እሷም እየሮጠች ወደ ቤቷ ስትመለስ አረዳህም ያለችው ዛፍ የወርቅ አፕል ተሞልቶ ነበር።
እሷም አውርዳለሁ ብላ ዛፍ ላይ ወጣች እሱም ተናዶ ሲወራጭ ወደቀች፡፡እናም አባቷ የመከራት ትዝ አላት እና ተፀፀተች፡፡እናም ወደ ቤቷ ተመለሰች ስንፍና እንደማይጠቅም ተማረች እናም በደስታ መኖር ጀመሩ።

