

በአንድ አነስተኛ መንደር የሚኖሩትንንሽ ሰዎች ሁለት ሰዎች ነበሩ ።ስማቸውም የሴቷ ኖራ የወንዱ ፊሊፕ የሚባሉ ሁለት ሰዎች ነበሩ ።ሁለቱም የተለያየ አስማት አላቸው።የኖራ አስማት ወደ ድራገን መቀየር ሲሆን ።የፊሊፕ ደግሞ የመሰውር አስማት ነበረው።
ሁለቱም በትምህርታቸው ታታሪና ተሸላሚ ናቸው። ለሰዎች ጥሩ መስራት ይፈልጋሉ ። አንድ በእነሱ አካባቢ የሚኖር ጫማ ስሪ ነበር ጫማ ሰሪው በአንድ ቀን እና በአንድ ለሊት ዉስጥ አንድ ጫማ ብቻ ነው የሚሰራው ለዛም ሰዎች አንዱን ጫማ ገዝተው ሲጨርሱ ሌላ ይጠይቁት ነበር ጫማ ሰሪውን የለም በማለት የመልስላቸው ነበረ።
ትንንሾቹ ሰዎች ይሔንንባዩጊዜ በጣም አዘኑ እነሱ አንድ ችሎታ ነበራቸው ። እሱም ጫማ ን በወርቅ የመስራት ችሎታ ነበር ።አንድ ቀን ማታ ጫማ ሰሪው ደክሞት ስለ ነበር እቤቱ ገባና ቁጭ ባለበት እንቅልፍ ወሰደው እናም የዛንማታ ጫማ መስራቱን ትውውቅ ባለቤቱም መኝታ ቤት ትታው ተኛች።
ትንንሾቹ ሰዎች ጫማ ሰሪው እና ባለቤቱ እንደተኙ አረጋግጠው ጫማ የሚሰራበትን መስኮት ከፍተው ገቡና ጫማ መስራት ጀመሩ።አንድ ሰዓት በማይሞላ ውስጥ ሰባት ጫማ ሠሩ ከዛም ውስጥ አንደኛው ጫማ የሚያወራው እናአስማተኛ ነበር ሰው ሳያያቸው ወጡ።
ጫማ ሰሪው በጠዋት ተነስቶ ጫማ የሚሰራበትን በር ከፈት ሲያደርገው የሚያወራው ጫማ«እንኳን ደህና መጣ» አለው:: የሚያወራው ጫማ ጫማ ሠሪው በድንጋጤ ቆሞ ቀረ ሚስቱን «ባለቤቴ ምን ሆነህ ነው» ስትል በጥያቄ አጣደፈችው እሱም «ነይቶሎ በይ» አላት መታ የሚያወራውን ጫማ የተሰሩትን ጫማ ስታያቸው በጣም ደስ አላት ወዲያውኑ«ይህንን ጫማ ማን ነው የሰራ ብላ ጠየቀችው አላውቅም አላት።
የሚያውራውን ጫማ ደበቁትና ሱቅ ከፍቱ አንድ በመንገድ ላይ የሚያልፍ ሰው ጫማ ዋቹን አይቷቸው ወደዳቸው እና ስድስቱንም ጫማ በውድ ዋጋ ገዛቸው ጫማ ስሪውም ተደስቶ በአንዴ ሀብታም ሆነ።
ጫማ የሚሰራበትንም ሱቅ አሳደሰ ከዛም ሱቁን ዘግቶ ወደ ገበያ ወጣና የቤት አስቤዛ ገዝቶ ወደ ቤቱ ገባ ሚስቱም «ጫማዎቹ ተሸጡ» አለችው «አዎ» አላት ስለመሸ እራት በሉና ተኙ።
ትናንሾቹ ሰዎችም እንደተለመደው በመስኮቱ ዘለው ገብቶ የተለመደውን የጫማ ስራ ጀመሩ። የጫማ ሰሪው ሚስቱም እንቅልፍ አልወሰዳትም ነበር።ሲያወሩ ሰማቻቸው ቀስ ብላ ከአልጋ ላይ በቀዳዳ ስትመለከት ሁለቱን የሚያምሩ ትንንሽ ሰዎችን አየቻቸው።
ጫማ ሠሪው «ሚስት ምን ሆነሽ ነው የምትንሿክኪው» ሲልጠየቃት።ከዛም «ናና» አለችው።እሱም በፍጥነት ካልጋ ላይ ወርዶ ጫማ ሳያጠልሷ ሲሄድ ባልየው የጫማ መስሪያውን መርፌ መሬት ላይ አስቀምጡት ስለነበር እግሩን ወጋው «ኡኡ »ሲል ጩኸቱ አቀለጠው።
ሁለት ትንንሽ ሰዎችም ደንግጠው ከቦታው ተሰወሩ ።ሴትየዋም እየሮጠች ውደ ባለቤቷ ጋር በመሄድ። ምን ይህ ነው ብትል ጠየቀችው እሱም የሆነውን አስረዳት ከዛም መርፌውን ከእግሩ ላይ ነቀለችለት አልኮል አርጋ በፍሻ ጠቀለለችለት።ደሙ አልቆም ሲል ጠራርጋ ሚስቱ አንድ ሀሳብ ብልጭ አለላት አስማተኛውን እና የሚያወራውን ጫማ አምጥታእግሩ ላይ አደረገችለት ወዲያውኑ እግሩን ተሻለው።
ከዛም ለሊት ላይ እንደተለመደው ትንንሾቹ ሰዎች ሲመጡ አመስግነው የተለያዩ ምግቦችን እና መጠጦች ሰጧቸው አስማተኛው ጫማም ትንንሾቹን ሰዎች ወደ ትላልቅ ሰዎች ለወጣቸው።
እነሱም በጣም ተደስተው አመስግነው፣አክብረው እና ስጦታ ሠጥተው አብረው መኖር ጀመሩ።

