የውቢት ውፍረት
ረድኤት ፍቅረ
ረድኤት ፍቅረ

አንዲት በገጠር ከተማ የምትኖር ውቢት የምትባል ወፍራም ልጅ ነበረች ፤ውፍረቷ ምንም መስሏት አያውቅም ነበር። አንድ ቀን ግን እቃ ልትገዛ ወደ ከተማ ስትሄድ አንድ ነገር አስተዋለች፤

1

ስታያቸው ሴቶቹ ሁሉ ሸንቃጦች ናችው፤ የለበሱት ልብስ ከሷ የተለየ ባይሆንም ልብሱ ግን እነሱ ላይ ያምርባቸዋል በዚህ እያዘነች እቃ መግዛቷን ትታ እየሄደች እያለ አንድ ፈርኒቸር ጋር ስትደርስ እራሷን በመስታወት አየች።

2

ሰዉነቷን ስታየው ሆዷ ብቻ ሶስት ፊት ነው፣ የሷ አንድ ጣት የሌሎቹን ሶስት ነው የሚያክለው። በዚህ እያዘነች ወደ ቤቷ ተመልሳ ከሰፈር ሰውም ከሌላም ሰው ለውፍረቷ መቀነሻ ዘዴ ስትጠይቅ ይሆናል ብለው ያሰቡትን ብዙ ዘዴ ነገሯት።

3

የነገሯትም ዘዴ ስራ ማብዛት፣ በቀን አንዴ በትንሹ መመገብ፣ እንዲሁም እየተጨነቅሽ ቀን በቀን ውፍረትሽን መለካት አሏት፤ እሷም ያሏትን እንዳለ እውነት መስሏት ያሏትን ሁሉ ስታደርግ ፤

4

በምግብ ማነስ፣ በስራ መብዛትና በጭንቀት ምክንያት ቅርፅ አልባ የባሰ ውፍረት መጣባት እሷም በጣም አዘነች፤ እንዲሁ እያዘነች እያለ አንድ ሄርሜላ የምትባል የአጎቷ ልጅ ከከተማ መጥታ እሷ ጋር አረፈች።

5

ውቢትም ከትንሽ ጊዜ በኋላ ያስጨነቃትን ነገር በሙሉ ለሄርሜላ ነገረቻት፤ ሄርሜላም ታዲያ ለዚህ ነው እንዴ የምትጨነቂው ብላ ካንቺ የሚጠበቀው፦

6

አለመጨነቅ፣ ዳይትመጠቀም እንዲሁም ጅም መስራት እና ሌሎችንም ቀስ ቀስ እያልሽ ትሰሪያለሽ ነይ ከኔ ጋር እንሂድና ከተማ ውስጥ እንኑር ስትላት፤

7

ውቢት ሄርሜላ ሰሪያለሽ ያለቻት አብዛኞቹ ነገሮች ባይገቧትም ግን እሺ በማለት አብረው ወደ ከተማ ሄዱና ጅም ምን እንደሆነ እንዴት እንደሚሰራ ካሳይቻት በኋላ ጂም ጀመረች።

8

ስለ ዳይትም አስረድታት ዳይት መጠቀም ጀመረች፣ጭንቀትም አቆመች።ይህንን ሁሉ ነገር ስታደርግ ያቺ የምትፈልጋት ሸንቃጣዋ ውቢት መጣችላት።

9

ልብሶችን እየለበሰች መስታወት ፊት ስትቆም በጣም ያምርባታል፤በዚህም ደስተኛ ሆነች።

10
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
የውቢት ውፍረት
Author - ረድኤት ፍቅረ
Illustration - ረድኤት ፍቅረ
Language - Amharic
Level - First paragraphs