ከበርቴው እና ሦስቱ ሌቦች
አርሴማ ንጉሴ
አርሴማ ንጉሴ

በድሩ ዘመን በአንድ አከባቢ አንድ ሀብታም በህሉ ፣በላሙ፣በከብቱ፣በንብረቱ እና በማንኛውም ሁሉ የደስደስ ያለው ከበርቴ ነበር ይባላል።

1

ነገር ግን ከሌላ አካባቢ የመጡት ሶስቱ ሌቦች ስለ ከበርቴ ሰምተው ስለ ከበርቴው ማጣራት ጀመሩ ከበቴ ማጣራት ጀመሩ ከበርቴ ከጓደኛቸው አቶ በላቸው ጋር ሲመካከሩ ወደ ክፍለሀገር እንደሚሄድ ለአቶ በላቸው ነገራቸው በዛ ሰዓት የሰሙት ሶስቱ ሌቦች እንዲህ ሲሉ ተመካከሩ።

2

እሱ ሲሄድ በሌሊት ከቤቱ ገብተን ንብረቱንና ገንዘቡ እንውሰድሲሉ ተመካከሩ።በሄደበት እለት ከቤቱ ገብተው ገንዘቡን ንብረቱን ይዘው ወደ ጫካ ገቡ።ከዚያም ሦስተኛ ጓደኛቸው ወደ ከተማ ሄዶ ምግብ እንደመጣላቸው ላኩት።

3

ሶስተኛ ጓደኛቸው ከሄደ በኋላ እንዲህ ሲሉ ተመካክሩ ሶስተኛ ጓደኛችን ሳንጨመር ያለውን ነገር ብንከፋፈል ብዙ ድርሻ ይኖረናል ብለው ተመካከሩ።ሦስተኛ ጓደኛቸውም እንዲህ ሲል አሰበ።ሁለቱ ጓደኞቼን ሳልጨምር ገንዘቡ የኔ ይሆናል እንዲህ ሲል ራሱን ጠየቀ አሀ እኔ በልቼ ስለ መሄድ በዚህ መርዝ ጓደኞቼን መግደል እችላለሁ ብሎ አሰበ።

4

እነሱም ሲመጣ ከአንድ ዛፍ ስር ተደብቀን በዱላ ጭንቅላቱ መተን ገለነው ገንዘቡን መውሰድ እንችላለን ሲሉ ተመካከሩ።እሱም ድርሻውን በልቶ ለነሱ የሚወስድላቸው ምግብ ላይ መርዝ ጨምሮ መጓዝ ጀመረ።እነሱም ከአንድ ዛፍ ስር ቆመው በእጃቸው ዱላ ይዘው እየጠበቁም ነበር።ከተደበቁበት ቦታው ሲደርስ በያዙት ዱላ ቀጥቅጠው ገደሉት።

5

የመጣውን ምግብ በተመገቡ ጊዜ ከግማሽ ሰዓት በኋላ እየተጨረጨሩ ሞቱ በጫካውም ሶስቱ ሌቦች ሬሳቸው ተገኘ ንብረቱ ለባለሃብቱ ተመለሰለት።

6
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ከበርቴው እና ሦስቱ ሌቦች
Author - አርሴማ ንጉሴ
Illustration - አርሴማ ንጉሴ
Language - Amharic
Level - First paragraphs