ጀግናው ውሻ
ረድኤት ሲሳይ
ረድኤት ሲሳይ

በአንድ አካባቢ ውስጥ የሚኖር አንድ ቦቢ የሚባል ተንኮለኛ ውሻ ነበር።

1

ውሻውም ለአካባቢው ማህበረሰብና ለአሳዳጊዎቹ ተንኮለኛና ውሸታም ነው።ለዛም በጣም ይናደዱበታል።ነገር ግን የአሳዳጊዎቹ ልጅ በጣም ይወደዋል።

2

የአካባቢው ማህበረሰብም በዚህ ሁኔታ እየተናደዱ አሳዳጊዎቹን እንደዚህ አሏቸው ውሻችሁን ቦቢን በስረአቱ ያዙት። ተንኮለኛ ከመሆኑ የተነሳ ቤታችን እየመጣ ልጆቻችን እያስለቀስ ነው። ስለዚህ ውሻችሁን ወደዛ ከመጣላችን በፊት ያዙት አሏቸው።በዚህም በጣም አዘኑ።

3

አንድ ቀንም እንዲህ ሲሉ አሰቡ።ለምን ውሻችንን ሌላ ቦታ አንስደውም ማለት ከዚህ ራቅ ያለ ቦታ አለች ሚስቱ።ባልየውም እኔም እያሰብኩኝ ነበር አላት።

4

በቀጣዩም ቀን ቦቢን አሰናብተው ከቤታቸው ራቅ ያለ ቦታ ወሰዱት። እሱም በጣም አዝኖ አለቀሰ።

5

አሳዳጊዎቹ ልጅ ውሻውን ይወደው ስለነበረ ወላጆቹ ሳያዩት ቦቢን ተከትሎት ነበረ እየተከተለውም እያለ የሆነ ጉድጓድ ውስጥ ሲገባ በጣም ደነገጠ። ውሻውም ይቅርታ ካደረጉልኝ ብሎ አስቦ ለመመለስም ወሰነ። እየሄደ እያለ የሆነ ድምፅ ሲሰማ ወዳለበት ሄደ። ሲሄድም የአሳዳጊዎቹ ልጅ ነበር። ቦቢም በጣም ደነገጠ።

6

ውሻውም ተስፋ ሳይቆርጥ ደጋግሞ ለፋ፣ጣረ በስተመጨረሻም ተሳክቶለት ልጁን አውጥቶት ወደ ቤት ይዞት ሄደ።

7

የልጁም ቤተሰቦች እየፈለጉት ስለነበረ ሲያዩት ተደናግጠው ሮጠው ቦቢንም ልጃቸውንም አቀፏቸው። ቦቢም ይቅርታ ጠይቆ ለራሱ እንዲህ አለ ከዚህ በሗላ ሰዎችን ማስከፋት የለብኝም አለ።

8
You are free to download, copy, translate or adapt this story and use the illustrations as long as you attribute in the following way:
ጀግናው ውሻ
Author - ረድኤት ሲሳይ
Illustration - ረድኤት ሲሳይ
Language - Amharic
Level - First paragraphs